Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሉቃስ 18:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ደቀ መዛሙርቱ ግን ከዚህ ሁሉ ነገር አንዱንም አልተረዱም፤ የንግግሩም ምሥጢር ተሰውሮባቸው ስለ ነበር ምን ማለቱ እንደ ሆነ አላወቁም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ደቀ መዛሙርቱ ግን ከዚህ ሁሉ የተረዱት አንድም ነገር አልነበረም፤ አባባሉም ተሰውሮባቸው ነበር፤ ስለ ምን እንደ ተናገረም አላወቁም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 እነርሱም ከዚህ ነገር ምንም አላስተዋሉም፤ ይህም ንግግር ተሰውሮባቸው ነበር፤ የተናገረውንም አላወቁም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 እነ​ርሱ ግን፤ ከተ​ና​ገ​ራ​ቸው ያስ​ተ​ዋ​ሉት የለም፤ ይህ ነገር ከእ​ነ​ርሱ የተ​ሰ​ወረ ነበ​ርና፤ የተ​ና​ገ​ረ​ው​ንም አያ​ው​ቁም ነበ​ርና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 እነርሱም ከዚህ ነገር ምንም አላስተዋሉም፥ ይህም ቃል ተሰውሮባቸው ነበር፥ የተናገረውንም አላወቁም።

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 18:34
9 Referencias Cruzadas  

እነርሱ ግን ይህን ነገር አላስተዋሉም፤ የንግግሩም ምሥጢር ተሰውሮባቸው ነበር፤ እንዳይጠይቁትም ፈሩ።


ደቀ መዛሙርቱ ግን ይህ ነገር አልገባቸውም፤ እንዳይጠይቁትም ፈሩ።


ደቀ መዛሙርቱ ይህ ነገር በመጀመሪያ አልገባቸውም ነበር፤ ግን ኢየሱስ በክብር ወደ ሰማይ ባረገ ጊዜ ይህ ነገር ስለ እርሱ እንደ ተጻፈና ለእርሱም እንደ ተደረገለት አስታወሱ።


ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤ እነርሱ ግን የተናገረውን አላስተዋሉም።


ከዚህ በኋላ ቅዱሳት መጻሕፍትን ማስተዋል እንዲችሉ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው።


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የማታስተውሉና ነቢያት የተናገሩትንም ሁሉ ከማመን ልባችሁ የዘገየ!


እነርሱ ግን እርሱ የተናገረውን አላስተዋሉም።


ከገረፉትም በኋላ ይገድሉታል፤ ነገር ግን በሦስተኛው ቀን ከሞት ይነሣል።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios