ማርቆስ 5:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ኢየሱስም መጥተው ያ በርኩሳን መናፍስት ተይዞ የነበረው ሰው ከአእምሮው ሕመም ድኖ፥ ልብሱን ለብሶ፥ ተቀምጦም ባዩት ጊዜ ደነገጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ኢየሱስም በመጡ ጊዜ፣ የአጋንንት ሰራዊት ሌጌዎን ዐድረውበት የነበረው ሰው፣ ልብስ ለብሶና አእምሮው ተመልሶለት በዚያ ተቀምጦ አዩት፤ ፈሩም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ኢየሱስም በመጡ ጊዜ፥ የአጋንንት ሠራዊት አድረውበት የነበረው ሰው፥ ልብስ ለብሶና አእምሮው ተመልሶለት ተቀምጦ አዩት፤ ፍርሃትም አደረባቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ኢየሱስም መጡ፤ አጋንንትም ያደሩበትን ሌጌዎንም የነበረበትን ሰው ተቀምጦ ለብሶም ልቡም ተመልሶ አዩና ፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ኢየሱስም መጡ፥ አጋንንትም ያደሩበትን ሌጌዎንም የነበረበትን ሰው ተቀምጦ ለብሶም ልቡም ተመልሶ አዩና ፈሩ። |
ደግሞስ አንድ ሰው አስቀድሞ ኀይለኛውን ሳያስር ወደ ኀይለኛው ቤት ገብቶ ንብረቱን መዝረፍ እንዴት ይችላል? ኀይለኛውን ካሰረው በኋላ ግን በእርግጥ ንብረቱን ሊዘርፍ ይችላል።
ዝናው በሶርያ አገር ሁሉ ስለ ተሰማ፥ ሰዎች በልዩ ልዩ በሽታና ደዌ የሚሠቃዩትን፥ ርኩሳን መናፍስት ያደሩባቸውን፥ የሚጥል በሽታ ያለባቸውንና ሽባዎችንም ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤ እርሱም ፈወሳቸው።
ብዙ ጊዜ በእግር ብረትና በሰንሰለት ይታሰር ነበር፤ ነገር ግን ሰንሰለቱን እየበጣጠሰና እግር ብረቱንም እየሰባበረ ይጥል ነበር፤ ስለዚህ ይዞ ሊያቆመው የሚችል ማንም አልነበረም።
ኢየሱስ ከጀልባ ወደ ምድር በወረደ ጊዜ አጋንንት ያደሩበት አንድ ሰው ከከተማ ወጥቶ ተገናኘው፤ ይህ ሰው ልብሱን ከጣለ ብዙ ጊዜው ነበር፤ የሚኖረውም በመቃብር ቦታ እንጂ በቤት ውስጥ አልነበረም።
ሳሙኤልም እግዚአብሔር ያዘዘውን ለማድረግ ወደ ቤተልሔም ሄደ፤ እዚያም እንደ ደረሰ የከተማይቱ መሪዎች በፍርሃት እየተንቀጠቀጡ ወደ ሳሙኤል ቀርበው “አመጣጥህ ለሰላም ነውን?” ሲሉ ጠየቁት።