Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 13:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ከዚህ በኋላ ዳዊት እግዚአብሔርን እጅግ ስለ ፈራ “እንግዲህ ይህን የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ቤቴ እንዴት መውሰድ እችላለሁ?” አለ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ዳዊት በዚያ ዕለት እግዚአብሔርን ስለ ፈራ፣ “ታዲያ የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ እኔ እንዴት ማምጣት እችላለሁ?” አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በዚያም ቀን ዳዊት፦ “የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ እኔ እንዴት አመጣለሁ?” ብሎ እግዚአብሔርን ፈራ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በዚ​ያም ቀን ዳዊት፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ወደ እኔ እን​ዴት አመ​ጣ​ለሁ?” ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈራ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 በዚያም ቀን ዳዊት “የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ እኔ እንዴት አመጣለሁ?” ብሎ እግዚአብሔርን ፈራ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 13:12
12 Referencias Cruzadas  

“በውኑ እግዚአብሔር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ ሰማያት፥ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ሊይዝህ አይችልም፤ እኔ የሠራሁት ይህ ቤተ መቅደስማ ምንኛ ያንስ?


ያም ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ “ፔሬጽ ዑዛ” ተብሎ ይጠራል፤ እግዚአብሔር ተቈጥቶ ዑዛን ስለ ገደለው ዳዊት እጅግ ተበሳጨ።


ስለዚህም ዳዊት ታቦቱን ወደ ኢየሩሳሌም በመውሰድ ፈንታ የጋት ከተማ ነዋሪ በሆነው፥ ዖቤድኤዶም ተብሎ በሚጠራው ሰው ቤት ተወው።


ነገር ግን ዳዊት የእግዚአብሔርን መልአክ ሰይፍ ስለ ፈራ ወደዚያ ሄዶ እግዚአብሔርን ለመጠየቅ አልቻለም።


አንተን ከመፍራቴ የተነሣ ሰውነቴ ተንቀጠቀጠ፤ ፍርድህንም እጅግ ፈራሁት።


እኔም “እነሆ አንደበቶቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል የምኖር፥ አንደበቴም የረከሰብኝ ሰው ነኝ፤ ንጉሡን የሠራዊት አምላክን በዐይኖቼ አይቼአለሁና መጥፋቴ ስለ ሆነ ወዮልኝ!” አልኩ።


አንድ መክሊት የተቀበለውም ቀርቦ፥ ‘ጌታ ሆይ! ካልዘራህበት የምታጭድ፥ ካልበተንክበት የምትሰበስብ፥ ጨካኝ ሰው መሆንክን ዐውቃለሁ፤


ስለዚህም የቤትሼሜሽ ሰዎች “በዚህ ቅዱስ አምላክ በእግዚአብሔር ፊት ማን መቆም ይችላል? ታቦቱስ ከእኛ ወጥቶ ወደ ማን ይሄዳል?” አሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos