“በሳምንት ስድስት ቀን ሥራህን ሁሉ ሥራ፤ በሰባተኛው ቀን ግን ምንም ሥራ አትሥራበት፤ በዚህ ዐይነት አገልጋዮችህና ለአንተ የሚሠሩ መጻተኞች፥ እንዲሁም በሬህና አህያህ ዕረፍት አድርገው ይዋሉ።
ማርቆስ 2:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግሞም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “ሰንበት ለሰው ተሠራ እንጂ ሰው ለሰንበት አልተፈጠረም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም እንዲህ አላቸው፤ “ሰንበት ለሰው ተፈጠረ እንጂ፣ ሰው ለሰንበት አልተፈጠረም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞ “ሰንበት ስለ ሰው ተፈጥሯል እንጂ ሰው ስለ ሰንበት አልተፈጠረም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞ “ሰንበት ስለ ሰው ተፈጥሮአል እንጂ ሰው ስለ ሰንበት አልተፈጠረም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞ፦ ሰንበት ስለ ሰው ተፈጥሮአል እንጂ ሰው ስለ ሰንበት አልተፈጠረም፤ |
“በሳምንት ስድስት ቀን ሥራህን ሁሉ ሥራ፤ በሰባተኛው ቀን ግን ምንም ሥራ አትሥራበት፤ በዚህ ዐይነት አገልጋዮችህና ለአንተ የሚሠሩ መጻተኞች፥ እንዲሁም በሬህና አህያህ ዕረፍት አድርገው ይዋሉ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በተቀደሰው ቀኔ የራሳችሁን ጥቅም በማሳደድ ሰንበቴን ከመሻር ብትቈጠቡ፥ ሰንበቴን አስደሳች፥ የተከበረውንም የእኔን የእግዚአብሔርን ቀን የተከበረ ቀን ብትሉት፥ የግል ፍላጎታችሁንና የግል ጉዳያችሁን ተግባራዊ ለማድረግ በራሳችሁ አካሄድ መመራትን ትታችሁ ሰንበቴን ብታከብሩ፥
እኔ ከእናንተ ጋር ለገባሁት ቃል ኪዳን ምልክት ይሆንላችሁ ዘንድ፥ እንዲሁም እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንኩ ያስታውሳችሁ ዘንድ ሰንበትን የተቀደሰ ቀን አድርጉት።
በዚህ ጊዜ ኢየሱስ “እስቲ ልጠይቃችሁ፤ ለመሆኑ በሰንበት ቀን የተፈቀደው መልካም ማድረግ ነውን? ወይስ ክፉ? ነፍስን ማዳን ነውን ወይስ ማጥፋት?” አላቸው።
እንግዲህ በሙሴ አማካይነት የተሰጠው ሕግ እንዳይሻር በሰንበት ቀን ሰው የሚገረዝ ከሆነ ታዲያ፥ እኔ በሰንበት ቀን የሰውን ሁለንተና በመፈወሴ ስለምን ትቈጣላችሁ?
ሰባተኛው ቀን ግን ለእኔ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ የዕረፍት ቀን ነው፤ በዚያን ቀን ምንም ዐይነት ሥራ አትሥራ፤ አንተም ሆንክ ልጆችህ፥ አገልጋዮችህም ሆኑ እንስሶችህ በአገርህ ውስጥ የሚኖሩ መጻተኞችም ቢሆኑ ምንም ሥራ አትሥሩበት፤ አገልጋዮችህም ልክ እንደ አንተው ዕረፍት ያድርጉ።