ማርቆስ 2:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከጥቂት ቀን በኋላ ኢየሱስ ወደ ቅፍርናሆም ተመልሶ መጣ፤ እዚያ በቤት ውስጥ መሆኑ ተሰማ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ ከጥቂት ቀን በኋላ ወደ ቅፍርናሆም እንደ ተመለሰ፣ ወደ ቤት መግባቱን ሕዝቡ ሰማ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጥቂት ቀን በኋላ ወደ ቅፍርናሆም ገባ፤ በቤት ውስጥ እንዳለም ተሰማ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከጥቂት ቀን በኋላ ወደ ቅፍርናሆም ደግሞ ገብቶ በቤት እንደ ሆነ ተሰማ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከጥቂት ቀን በኋላ ወደ ቅፍርናሆም ደግሞ ገብቶ በቤት እንደ ሆነ ተሰማ። |
ይሁን እንጂ ሰውየው ከዚያ ወጥቶ ይህን ነገር ለሰው ሁሉ ማውራት ጀመረ። በዚህም ምክንያት ኢየሱስ ወደ ማናቸውም ከተማ በግልጥ መግባት አልቻለም። ነገር ግን ከከተማ ውጪ ሰው በሌለበት ቦታ ይኖር ነበር፤ ሆኖም ሰዎች ከየስፍራው ወደ እርሱ ይመጡ ነበር።
ኢየሱስ ከዚያ ተነሥቶ በጢሮስ ከተማ አጠገብ ወዳለው መንደር ሄደ፤ ወደ አንድ ቤትም ገብቶ እዚያ መኖሩን ማንም ሰው እንዳያውቅ ፈለገ፤ ይሁን እንጂ ሊሰወር አልተቻለውም።
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “ ‘አንተ ሐኪም፥ እስቲ ራስህን አድን፥’ የሚለውን ምሳሌ እንደምትጠቅሱብኝ እርግጠኛ ነኝ፤ እንዲሁም ‘በቅፍርናሆም አድርገሃል ሲሉ የሰማነውን ሁሉ፥ እዚህም በገዛ አገርህ አድርግ’ ትሉኛላችሁ።
እርሱም ኢየሱስ ከይሁዳ ምድር ወደ ገሊላ መምጣቱን ሰምቶ ወደ እርሱ ሄደ፤ ወደ ቅፍርናሆም እንዲወርድና በጠና ታሞ ሊሞት የተቃረበውን ልጁን እንዲፈውስለት ኢየሱስን ለመነው።