የሠራዊት አምላክ፥ የእስራኤል ንጉሥና አዳኝ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የመጀመሪያውም የመጨረሻውም እኔ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም።
ማርቆስ 15:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ መሲሑ የእስራኤል ንጉሥ ከሆነ እስቲ አሁን ከመስቀል ይውረድ፤ እኛም እንይና እንመንበት!” እንዲሁም ከእርሱ ጋር የተሰቀሉት ወንበዴዎች ይሰድቡት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አይተን እናምን ዘንድ ይህ ክርስቶስ፣ ይህ የእስራኤል ንጉሥ እስኪ ከመስቀል ይውረድ።” ከርሱ ጋራ የተሰቀሉትም እንደዚሁ የስድብ ናዳ ያወርዱበት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አይተን እናምን ዘንድ ይህ ክርስቶስ፥ ይህ የእስራኤል ንጉሥ እስቲ ከመስቀል ይውረድ።” ከእርሱ ጋር የተሰቀሉትም እንደዚሁ የስድብ ናዳ ያወርዱበት ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አይተን እናምን ዘንድ የእስራኤል ንጉሥ ክርስቶስ አሁን ከመስቀል ይውረድ፤” አሉ። ከእርሱም ጋር የተሰቀሉት ይነቅፉት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አይተን እናምን ዘንድ የእስራኤል ንጉሥ ክርስቶስ አሁን ከመስቀል ይውረድ አሉ። ከእርሱም ጋር የተሰቀሉት ይነቅፉት ነበር። |
የሠራዊት አምላክ፥ የእስራኤል ንጉሥና አዳኝ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የመጀመሪያውም የመጨረሻውም እኔ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም።
እግዚአብሔር በእናንተ ላይ ያስተላለፈውን የቅጣት ፍርድ አንሥቶላችኋል፤ ጠላቶቻችሁንም አስወግዶላችኋል፤ የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር በመካከላችሁ ነው፤ ከእንግዲህ ወዲህ ጥፋት ይደርስብናል ብላችሁ አትፈሩም።
ጽዮን ሆይ! ደስ ይበልሽ! ኢየሩሳሌም ሆይ! በደስታ እልል በይ! እነሆ ንጉሥሽ ትሑት ሆኖ፥ በአህያይቱ ማለትም በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ፥ በድል አድራጊነት ወደ አንቺ ይመጣል።
እንግዲህ ከአብርሃም እስከ ዳዊት ዐሥራ አራት ትውልድ፥ ከዳዊት እስከ ባቢሎን ምርኮ ዐሥራ አራት ትውልድ፥ ከባቢሎን ምርኮ እስከ መሲሕ ዐሥራ አራት ትውልድ ነው።