ማርቆስ 15:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንጀሉንም ለማመልከት “የአይሁድ ንጉሥ” የሚል ጽሑፍ ተጽፎ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የክሱ ጽሑፍም፣ የአይሁድ ንጉሥ የሚል ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የክሱ ጽሑፍም፥ “የአይሁድ ንጉሥ” የሚል ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የክሱ ጽሕፈትም “የአይሁድ ንጉሥ” የሚል ተጽፎ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የክሱ ጽሕፈትም፦ የአይሁድ ንጉሥ የሚል ተጽፎ ነበር። |
የእነርሱ ዕቅድ ግን ይህ አይደለም፤ ይህም ጉዳይ በሐሳባቸው ውስጥ የለም፤ የእነርሱ ዓላማ ግን ጥቂቶቹን ሳይሆን ብዙዎችን ሕዝቦች ለማጥፋት ነው።
በመጨረሻ የሚሆነውን ነገር ከመጀመሪያው ጀምሬ ተናግሬአለሁ፤ ወደፊት ምን እንደሚሆን ከጥንት ጀምሬ ገልጬአለሁ፤ ዓላማዬ የጸና ይሆናል፤ የምፈቅደውንም አደርጋለሁ።
ጽዮን ሆይ! ደስ ይበልሽ! ኢየሩሳሌም ሆይ! በደስታ እልል በይ! እነሆ ንጉሥሽ ትሑት ሆኖ፥ በአህያይቱ ማለትም በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ፥ በድል አድራጊነት ወደ አንቺ ይመጣል።
እርሱ መሲሑ የእስራኤል ንጉሥ ከሆነ እስቲ አሁን ከመስቀል ይውረድ፤ እኛም እንይና እንመንበት!” እንዲሁም ከእርሱ ጋር የተሰቀሉት ወንበዴዎች ይሰድቡት ነበር።
ነገር ግን እግዚአብሔር አምላክህ እርሱን ማዳመጥ አልፈለገም፤ ይልቁንም እግዚአብሔር አንተን ስለሚወድህ መርገሙን ወደ በረከት ለወጠው። እግዚአብሔር እናንተን ይወዳችኋል።