ማርቆስ 14:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የፋሲካውን በግ በሚያርዱበት በቂጣ በዓል መጀመሪያ ቀን፥ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ ቀርበው፦ “የፋሲካን ራት ለመብላት ወዴት ሄደን እንድናዘጋጅልህ ትፈልጋለህ?” ሲሉ ጠየቁት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የፋሲካ በግ በሚታረድበት በቂጣ በዓል የመጀመሪያው ቀን፣ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ ቀርበው፣ “የፋሲካ እራት የት እንድናዘጋጅልህ ትፈልጋለህ?” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የፋሲካ በግ በሚታረድበት በቂጣ በዓል የመጀመሪያው ቀን፥ ደቀመዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ ቀርበው፥ “የፋሲካ እራት የት እንድናዘጋጅልህ ትፈልጋለህ?” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የፋሲካን በግ በሚያርዱበት በቂጣ በዓል መጀመሪያ ቀን ደቀ መዛሙርቱ “ፋሲካን ትበላ ዘንድ ወዴት ሄደን ልናሰናዳ ትወዳለህ?” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፋሲካን በሚያርዱበት በቂጣ በዓል መጀመሪያ ቀን ደቀ መዛሙርቱ፦ ፋሲካን ትበላ ዘንድ ወዴት ሄደን ልናሰናዳ ትወዳለህ? አሉት። |
ሙሴም ለሕዝቡ እንዲህ አለ፦ “ይህ ቀን በባርነት ስትገዙ የኖራችሁበትን የግብጽን ምድር ለቃችሁ የወጣችሁበት ስለ ሆነ ይህን ቀን አስታውሱ፤ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ በመታደግ ያወጣችሁ በዚህ ቀን ነው፤ ስለዚህ በዚህ ቀን እርሾ የነካው እንጀራ አትብሉ።
ኢየሱስ ግን “የጽድቅን ሥራ ሁሉ በዚህ መንገድ መፈጸም ስለሚገባን፥ አሁንስ ተው፤ እንዲሁ ይሁን” ሲል መለሰለት። ዮሐንስም በነገሩ ተስማምቶ ኢየሱስን አጠመቀው።
የአይሁድ የፋሲካና የቂጣ በዓል ሊከበር ሁለት ቀን ቀርቶት ነበር፤ የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን ኢየሱስን በተንኰል ይዘው የሚገድሉበትን ዘዴ ይፈልጉ ነበር።
እርሱም ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን እንዲህ ሲል ላካቸው፤ “ወደ ከተማ ሂዱ፤ እዚያም የውሃ እንሥራ የተሸከመ ሰው ታገኛላችሁ፤ እርሱን ተከተሉት፤