ማርቆስ 10:48 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብዙዎቹ “ዝም በል!” ብለው ገሠጹት፤ እርሱ ግን “የዳዊት ልጅ ሆይ! እባክህ ማረኝ!” እያለ ይበልጥ ጮኸ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብዙዎችም ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እርሱ ግን፣ “የዳዊት ልጅ ሆይ፤ ማረኝ!” እያለ የባሰ ጮኸ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብዙዎችም ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እርሱ ግን፥ “የዳዊት ልጅ ሆይ፤ ማረኝ!” እያለ የባሰ ጮኸ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብዙዎችም ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እርሱ ግን “የዳዊት ልጅ ሆይ! ማረኝ” እያለ አብዝቶ ጮኸ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብዙዎችም ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እርሱ ግን፦ የዳዊት ልጅ ሆይ ማረኝ እያለ አብዝቶ ጮኸ። |
ኢየሱስ ገና ይህን በመናገር ላይ ሳለ ከምኲራብ አለቃው ቤት የመጡ ሰዎች የምኲራብ አለቃውን፦ “ልጅህ ሞታለች፤ እንግዲህ ስለምን መምህሩን ታደክመዋለህ?” አሉት።
ቀድመው እፊት እፊት ይሄዱ የነበሩት ሰዎች፦ “ዝም በል!” ብለው ገሠጹት። እርሱ ግን ድምፁን በይበልጥ ከፍ አድርጎ፦ “የዳዊት ልጅ ሆይ! እባክህ ማረኝ!” ይል ነበር።
ኢየሱስ ሰው ሆኖ በዚህ ምድር በኖረበት ጊዜ ከሞት ሊያድነው ወደሚችል አምላክ በታላቅ ጩኸትና በብዙ እንባ ጸሎትንና ልመናን አቀረበ፤ በትሕትና ራሱን ታዛዥ በማድረጉ እግዚአብሔር ጸሎቱን ሰማው።