Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ማቴዎስ 19:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 በዚያን ጊዜ እጁን በላያቸው ላይ ጭኖ እንዲጸልይላቸው ሰዎች ሕፃናትን ወደ ኢየሱስ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱ ግን ሰዎቹን ገሠጹአቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ከዚያም እጆቹን በላያቸው ላይ እንዲጭንባቸውና እንዲጸልይላቸው ሕፃናትን ወደ እርሱ አቀረቧቸው። ደቀ መዛሙርቱ ግን ሕፃናቱን ያመጡትን ሰዎች ገሠጿቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በዚያን ጊዜ እጆቹን ጭኖ እንዲጸልይላቸው ሕፃናትን ወደ እርሱ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱም ገሠጹአቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በዚያን ጊዜ እጁን እንዲጭንባቸውና እንዲጸልይ ሕፃናትን ወደ እርሱ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱም ገሠጹአቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በዚያን ጊዜ እጁን እንዲጭንባቸውና እንዲጸልይ ሕፃናትን ወደ እርሱ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱም ገሠጹአቸው።

Ver Capítulo Copiar




ማቴዎስ 19:13
15 Referencias Cruzadas  

የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ፥ ጌታ አምላካችን ወደ እርሱ ለሚጠራቸው፥ በሩቅ ላሉትም ሁሉ ነው።”


ክርስቲያን ያልሆነ ባል ክርስቲያን በሆነች ሚስቱ ምክንያት የእግዚአብሔር ወገን ይሆናል፤ ክርስቲያን ያልሆነች ሚስትም ክርስቲያን በሆነው ባልዋ ምክንያት የእግዚአብሔር ወገን ትሆናለች፤ እንደዚህ ካልሆነማ ልጆቻችሁ የእግዚአብሔር ሰዎች ሊሆኑ አይችሉም፤ በዚህ ዐይነት ከኖራችሁ ግን ልጆቻችሁ የእግዚአብሔር ሰዎች ናቸው።


ሕዝቡም “ዝም በሉ!” ብለው ገሠጹአቸው፤ እነርሱ ግን “የዳዊት ልጅ ጌታ ሆይ! እባክህ ማረን!” እያሉ አብዝተው ጮኹ።


ጴጥሮስ ግን ኢየሱስን ለብቻ ገለል አድርጎ፦ “ጌታ ሆይ! ከቶ አይሆንም! ይህ ነገር ከቶ አይደርስብህም!” እያለ ይገሥጸው ጀመር።


አንድ ዓላማ እንዲኖራቸው አደርጋለሁ፤ ይኸውም ለእነርሱና ለልጆቻቸው ሁሉ መልካም ነገር እንዲሆንላቸው ዘወትር ያከብሩኝ ዘንድ ነው።


ጡት ካስጣለችውም በኋላ ወደ ሴሎ ይዛው ወጣች፤ ከእርሱም ጋር የሦስት ዓመት ኰርማ ዐሥር ኪሎ ዱቄትና አንድ አቁማዳ ሙሉ የወይን ጠጅ ይዛ ሄደች፤ ሳሙኤልንም ገና በልጅነቱ በሴሎ ወደሚገኘው ወደ እግዚአብሔር ቤት ወሰደችው፤


ጥቂት ጊዜ ካለፈ በኋላ “አባትህ ታሞአል” ተብሎ ለዮሴፍ ተነገረው፤ ስለዚህ ዮሴፍ ሁለቱን ልጆቹን ምናሴንና ኤፍሬምን ይዞ ያዕቆብን ለማየት ሄደ።


ጃንደረቦች ሆነው የተወለዱ አሉ፤ ሰው የሰለባቸውም አሉ፤ ለመንግሥተ ሰማይ ሲሉ ራሳቸውን እንደ ስልብ ያደረጉ አሉ፤ ስለዚህ ይህን ሊቀበል የሚችል ይቀበለው።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios