ማርቆስ 10:47 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም የሚያልፈው የናዝሬቱ ኢየሱስ መሆኑን ባወቀ ጊዜ “የዳዊት ልጅ ኢየሱስ ሆይ፥ እባክህ ራራልኝ!” እያለ ይጮኽ ጀመር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም የናዝሬቱ ኢየሱስ መሆኑን በሰማ ጊዜ፣ “የዳዊት ልጅ፣ ኢየሱስ ሆይ፤ ማረኝ!” እያለ ይጮኽ ጀመር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም የናዝሬቱ ኢየሱስ መሆኑን በሰማ ጊዜ፥ “የዳዊት ልጅ፥ ኢየሱስ ሆይ፤ ማረኝ” እያለ ይጮኽ ጀመር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የናዝሬቱ ኢየሱስም እንደ ሆነ በሰማ ጊዜ “የዳዊት ልጅ ኢየሱስ ሆይ!” ማረኝ እያለ ይጮኽ ጀመር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የናዝሬቱ ኢየሱስም እንደ ሆነ በሰማ ጊዜ፦ የዳዊት ልጅ ኢየሱስ ሆይ፥ ማረኝ እያለ ይጮኽ ጀመር። |
ከዚያም አንዲት ከነዓናዊት ሴት ወደ ኢየሱስ መጥታ፥ “የዳዊት ልጅ ጌታ ሆይ! ልጄ በርኩስ መንፈስ ተይዛ ትሠቃያለችና እባክህ ራራልኝ!” እያለች ጮኸች።
እነሆ፥ በመንገድ ዳር የተቀመጡ ሁለት ዕውሮች በዚያ በኩል የሚያልፈው ኢየሱስ መሆኑን በሰሙ ጊዜ፥ “ጌታ የዳዊት ልጅ ሆይ! እባክህ ማረን!” እያሉ ጮኹ።
ከሕዝቡም ፊት ለፊት ይሄዱ የነበሩትና ከኋላ ይከተሉ የነበሩት፥ “ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ ምስጋና ይሁን! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው! ሆሳዕና! ምስጋና በአርያም ለእግዚአብሔር ይሁን!” እያሉ ይጮኹ ነበር።
“የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ፥ አንተ ከእኛ ጋር ምን ጉዳይ አለህ? ልታጠፋን መጣህን? አንተ ማን እንደ ሆንክ እኔ ዐውቃለሁ፤ አንተ የእግዚአብሔር ቅዱስ ነህ።”
“እኔ ኢየሱስ ይህን ምስክርነት እንዲሰጣችሁ መልአኬን ለአብያተ ክርስቲያን ልኬአለሁ፤ እኔ የዳዊት የትውልድ ሐረግና ዘር ነኝ፤ የሚያበራ የንጋት ኮከብ ነኝ።”