Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ማርቆስ 10:46 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

46 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ኢያሪኮ ከተማ መጣ። አልፎም ከከተማው ወጥቶ በሚሄድበት ጊዜ እጅግ ብዙ ሕዝብ ይከተለው ነበር፤ በመንገድ ዳር ደግሞ የጤሜዎስ ልጅ የሆነ በርጤሜዎስ የሚባል አንድ ዕውር ተቀምጦ ይለምን ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

46 ከዚህ በኋላ ወደ ኢያሪኮ መጡ። ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ከብዙ ሕዝብ ጋራ ከኢያሪኮ ሲወጡ ዐይነ ስውሩ የጤሜዎስ ልጅ በርጤሜዎስ በመንገድ ዳር ተቀምጦ ይለምን ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

46 ከዚህ በኋላ ወደ ኢያሪኮ መጡ። ኢየሱስና ደቀመዛሙርቱ ከብዙ ሕዝብ ጋር ከኢያሪኮ ሲወጡ ዐይነ ስውሩ የጤሜዎስ ልጅ በርጤሜዎስ በመንገድ ዳር ተቀምጦ ይለምን ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

46 ወደ ኢያሪኮም መጡ። ከደቀ መዛሙርቱና ከብዙ ሕዝብ ጋር ከኢያሪኮ ሲወጣ የጤሜዎስ ልጅ ዕውሩ በርጤሜዎስ እየለመነ በመንገድ ዳር ተቀምጦ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

46 ወደ ኢያሪኮም መጡ። ከደቀ መዛሙርቱና ከብዙ ሕዝብ ጋር ከኢያሪኮ ሲወጣ የጤሜዎስ ልጅ ዕውሩ በርጤሜዎስ እየለመነ በመንገድ ዳር ተቀምጦ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




ማርቆስ 10:46
9 Referencias Cruzadas  

ኢየሱስ ወደ ኢያሪኮ በቀረበ ጊዜ አንድ ዕውር ምጽዋት እየለመነ በመንገድ ዳር ተቀምጦ ነበር፤


ጐረቤቶቹና ቀድሞ ሲለምን ያዩት የነበሩ ሰዎች፥ “ይህ ሰው ያ ተቀምጦ ይለምን የነበረው አይደለምን?” አሉ።


“ከዚህም በኋላ ድኻው ሰው ሞተ፤ መላእክትም ወደ አብርሃም አጠገብ ወሰዱት፤ እንዲሁም ሀብታሙ ሰው ሞተና ተቀበረ።


መላ ሰውነቱ በቊስል የተወረሰ አልዓዛር የሚባል አንድ ድኻ ደግሞ በሀብታሙ ቤት ደጃፍ ተኝቶ ነበር፤


ሲዘራም አንዳንዱ ዘር በመንገድ ዳር ወደቀና ወፎች መጥተው በሉት።


ኢየሱስ ወደ ኢያሪኮ ከተማ ገብቶ በዚያ በኩል አልፎ እየሄደ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios