ዳዊት ግን አቢሳንና ወንድሙን ኢዮአብን “ይህን አሳብ እንድታቀርቡ የጠየቃችሁ ማን ነው? ችግር ልታመጡብኝ ትፈልጋላችሁን? እነሆ፥ አሁን የእስራኤል ንጉሥ እኔ ነኝ፤ ደግሞም በዛሬው ዕለት ማንም እስራኤላዊ በሞት አይቀጣም” አላቸው።
ሉቃስ 9:55 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ግን ወደ እነርሱ መለስ ብሎ ገሠጻቸው። [እናንተ ከምን ዐይነት መንፈስ እንደ ሆናችሁ አታውቁም፤ የሰው ልጅ የመጣው የሰውን ሕይወት ለማዳን ነው እንጂ፥ ለማጥፋት አይደለም።] አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ ግን ዘወር ብሎ ገሠጻቸውና፣ እርሱና ደቀ መዛሙርቱ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ግን ዘወር ብሎ ገሠጻቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ግን ዘወር ብሎ፥ “ከምን መንፈስ እንደ ሆናችሁ አታውቁም” ብሎ ገሠጻቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ግን ዘወር ብሎ ገሠጻቸውና፦ ምን ዓይነት መንፈስ እንደ ሆነላችሁ አታውቁም፤ |
ዳዊት ግን አቢሳንና ወንድሙን ኢዮአብን “ይህን አሳብ እንድታቀርቡ የጠየቃችሁ ማን ነው? ችግር ልታመጡብኝ ትፈልጋላችሁን? እነሆ፥ አሁን የእስራኤል ንጉሥ እኔ ነኝ፤ ደግሞም በዛሬው ዕለት ማንም እስራኤላዊ በሞት አይቀጣም” አላቸው።
ኢዮብም “እንዴት የሞኝ ሴት ንግግር ትናገሪያለሽ? እግዚአብሔር መልካም ነገር ሲሰጠን በደስታ እንቀበላለን፤ ታዲያ፥ መከራ ሲያመጣብን በእርሱ ላይ ማጒረምረም ይገባናልን?” አላት። ኢዮብ ምንም እንኳ ይህ ሁሉ መከራና ሥቃይ ቢደርስበት በእግዚአብሔር ላይ ክፉ ነገር በመናገር ኃጢአት አልሠራም።
ኢየሱስ ግን ዞር ብሎ ጴጥሮስን፦ “አንተ ሰይጣን! ከኋላዬ ሂድ! አንተ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን ነገር ስለማታስብ ለእኔ እንቅፋት ነህ” አለው።
ደቀ መዛሙርቱ ያዕቆብና ዮሐንስ ይህን ባዩ ጊዜ፥ “ጌታ ሆይ! ከሰማይ እሳት ወርዶ እነዚህን ሰዎች ያቃጥላቸው ዘንድ እንድናዝዝ ትፈቅዳለህን?” አሉት።