እንዲህም አላቸው፤ “በጥሞና ትእዛዞቼን ብታዳምጡና በፊቴ መልካም የሆነውን ነገር በታዛዥነት ብታደርጉ፥ ኅጎቼንም ሁሉ ብትጠበቁ፥ በግብጻውያን ላይ ካመጣሁባቸው በሽታዎች በአንዱ እንኳ አልቀጣችሁም፤ ፈዋሻችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”
ሉቃስ 8:44 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋ ወደ ኢየሱስ መጥታ ከበስተኋላው ቀረበችና የልብሱን ጫፍ ነካች፤ ወዲያውኑ ደምዋ መፍሰሱን አቆመ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም ከበስተኋላው ተጠግታ የልብሱን ጫፍ ነካች፤ የሚፈስሰው ደሟም ወዲያውኑ ቆመ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከበስተኋላውም ቀርባ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፤ ወዲያውም ደምዋ መፍሰሱን አቆመ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀርባም በጌታችን በኢየሱስ በስተኋላው ቆመችና የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፤ ያንጊዜም የደምዋ መፍሰስ ቆመ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኋላውም ቀርባ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፥ የደምዋም ፈሳሽ በዚያን ጊዜ ቆመ። |
እንዲህም አላቸው፤ “በጥሞና ትእዛዞቼን ብታዳምጡና በፊቴ መልካም የሆነውን ነገር በታዛዥነት ብታደርጉ፥ ኅጎቼንም ሁሉ ብትጠበቁ፥ በግብጻውያን ላይ ካመጣሁባቸው በሽታዎች በአንዱ እንኳ አልቀጣችሁም፤ ፈዋሻችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”
እነሆ፥ ዐሥራ ሁለት ዓመት ሙሉ ደም እየመታት ትሠቃይ የነበረች አንዲት ሴት፥ በዚያን ጊዜ ከኢየሱስ በስተኋላ መጥታ የልብሱን ጫፍ በእጅዋ ነካች።
በየሄደበትም ስፍራ ሁሉ በመንደር፥ በከተማ፥ በገጠርም በሽተኞችን ወደ አደባባይ እያወጡ በእርሱ ፊት ያቀርቡአቸው ነበር፤ የልብሱንም ጫፍ እንኳ እንዲነኩ ይለምኑት ነበር፤ የነኩትም ሁሉ ይድኑ ነበር።
ከኢየሱስ በስተኋላ በእግሮቹ አጠገብ ቆማ እያለቀሰች እግሮቹን በእንባዋ ታርስና በጠጒርዋ ታብስ ነበር፤ እግሮቹን እየሳመች ሽቶ ትቀባቸው ነበር።
ዐሥራ ሁለት ዓመት ሙሉ ደም እየመታት የምትሠቃይ አንዲት ሴት ነበረች፤ እርስዋም ያላትን ገንዘብ ሁሉ ለሐኪሞች በመክፈል ጨርሳ ማንም ሊያድናት አልቻለም።
ኢየሱስም “ማን ነው የነካኝ?” ሲል ጠየቀ። ሁሉም “እኛ አልነካንህም፤” አሉ፤ ጴጥሮስም “መምህር ሆይ፥ ሕዝቡ እየተጋፋ ሲከተልህ እያየህ ማን ነው የነካኝ ትላለህን?” አለው።
በዚህም ምክንያት የጳውሎስን አካል የነካውን ልብስና መሐረብ እየወሰዱ በሽተኞቹን ሲያስነኩአቸው ከበሽታቸው ይፈወሱ ነበር፤ ርኩሳን መናፍስትም ይወጡላቸው ነበር።
ሰዎች ብዙ በሽተኞችን ወደ መንገድ እያወጡ በአልጋ ላይና በቃሬዛ ላይ ያስተኙአቸው ነበር፤ እንዲህም ያደረጉት ጴጥሮስ በዚያ በኩል ሲያልፍ ጥላው እንኳ በአንዳንዶቹ ላይ እንዲያርፍባቸው ነበር።