ሉቃስ 7:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጥበብ ትክክለኛነት በልጆችዋ ይረጋገጣል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጥበብ ግን ትክክለኛ መሆኗ በልጆቿ ሁሉ ዘንድ ተረጋገጠ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን የጥበብ መጽደቅ በልጆችዋ ሁሉ ተረጋገጠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጥበብም ከልጆችዋ ሁሉ ጸደቀች።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጥበብም ለልጆዋ ሁሉ ጸደቀች። |
ጥበብ ያላቸው እነዚህን ነገሮች ይረዳሉ፤ አስተዋዮችም ያውቋቸዋል፤ የእግዚአብሔር መንገድ ትክክል ነው፤ ጻድቃን ይሄዱበታል፤ ኃጢአተኞች ግን ይሰናከሉበታል።
የሰው ልጅ ደግሞ እየበላና እየጠጣ ቢመጣ፥ ‘እነሆ! ይህ መብልና መጠጥ የሚወድ ነው! የቀራጮችና የኃጢአተኞችም ወዳጅ ነው!’ አሉት። ሆኖም የጥበብ ትክክለኛነት ግን በሥራዋ ይረጋገጣል።”