የሁሉም ዕድል ፈንታው አንድ ዐይነት ነው፤ ይህም በዓለም እንደሚደረገው እንደማንኛውም ነገር ሁሉ እጅግ የከፋ ነው፤ ሰዎችም በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ አእምሮአቸው በክፋትና በእብደት የተሞላ ሆኖ በመጨረሻ ይሞታሉ።
ሉቃስ 6:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ግን በጣም ተቈጥተው በኢየሱስ ላይ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ተመካከሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈሪሳውያንና የሕግ መምህራን ግን በቍጣ ተሞሉ፤ በኢየሱስ ላይ ምን ማድረግ እንዳለባቸውም እርስ በርስ ተወያዩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱ ግን በቁጣ ተሞሉ፤ በኢየሱስም ላይ ምን እንደሚያደርጉበት እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱ ግን፥ እጅግ ተቈጡ፤ በጌታችን በኢየሱስም ምን እንድሚያደርጉበት እርስ በርሳቸው ተማከሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ቍጣ ሞላባቸው፥ በኢየሱስም ምን እንዲያደርጉበት እርስ በርሳቸው ተባባሉ። |
የሁሉም ዕድል ፈንታው አንድ ዐይነት ነው፤ ይህም በዓለም እንደሚደረገው እንደማንኛውም ነገር ሁሉ እጅግ የከፋ ነው፤ ሰዎችም በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ አእምሮአቸው በክፋትና በእብደት የተሞላ ሆኖ በመጨረሻ ይሞታሉ።
ኢየሱስ በዙሪያው ወዳሉት ሰዎች ሁሉ ከተመለከተ በኋላ እጀ ሽባውን፥ “እጅህን ዘርጋ!” አለው። እርሱም እጁን በዘረጋው ጊዜ ዳነለትና እንደ ሌላው እጅ ደኅና ሆነ።
ስለዚህ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን የሸንጎውን አባሎች ሰብስበው እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው ብዙ ተአምራት ስለሚያደርግ ምን ብናደርግ ይሻላል?
ብዙ ጊዜ በየምኲራቡ እንዲቀጡና በጌታ ላይ የስድብ ቃል እንዲናገሩ አስገድዳቸው ነበር፤ በእነርሱ ላይ በጣም ተቈጥቼም ወደ ሌሎች የውጪ አገር ከተሞች እንኳ ወጥቼ እየሄድኩ አሳድዳቸው ነበር።
ጴጥሮስና ዮሐንስ ግን እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፦ “ለእግዚአብሔር ከመታዘዝ ይልቅ ለእናንተ መታዘዝ በእግዚአብሔር ፊት ተገቢ ነውን? እስቲ እናንተ ራሳችሁ ፍረዱ።