ሉቃስ 4:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም ርኩሱን መንፈስ፥ “ዝም ብለህ ከእርሱ ውጣ!” ሲል ገሠጸው፤ ርኩሱ መንፈስ ሰውየውን በሕዝቡ ፊት ጣለውና ምንም ሳይጐዳው ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም፣ “ጸጥ በል፤ ከርሱም ውጣ!” ብሎ ገሠጸው። ጋኔኑም ሰውየውን በሕዝቡ ሁሉ ፊት ጣለውና ምንም ጕዳት ሳያደርስበት ለቅቆት ከርሱ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም፦ “ዝም በል፤ ከእርሱም ውጣ፤” ብሎ ገሠጸው። ጋኔኑም በመካከላቸው ጥሎት ምንም ሳይጐዳው ከእርሱ ወጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችን ኢየሱስም፥ “ዝም በልና ከእርሱ ውጣ” ብሎ ገሠጸው፤ ጋኔኑም በምኵራቡ መካከል ጣለውና ከእርሱ ወጣ፤ ነገር ግን ምንም አልጐዳውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም፦ ዝም በል ከእርሱም ውጣ ብሎ ገሠጸው። ጋኔኑም በመካከላቸው ጥሎት ሳይጐዳው ከእርሱ ወጣ። |
የእግዚአብሔርም መልአክ ሰይጣንን “አንተ ሰይጣን! እግዚአብሔር ይገሥጽህ! ኢየሩሳሌምን የሚወድ እግዚአብሔር ይገሥጽህ! ይህ ሰው እኮ ከእሳት ውስጥ ተርፎ እንደ ወጣ እንጨት ነው” አለው።
እርሱም “እናንተ እምነት የጐደላችሁ! ስለምን ትፈራላችሁ?” አላቸው። ከዚያም በኋላ ኢየሱስ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ፤ ታላቅ ጸጥታም ሆነ።
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “ ‘አንተ ሐኪም፥ እስቲ ራስህን አድን፥’ የሚለውን ምሳሌ እንደምትጠቅሱብኝ እርግጠኛ ነኝ፤ እንዲሁም ‘በቅፍርናሆም አድርገሃል ሲሉ የሰማነውን ሁሉ፥ እዚህም በገዛ አገርህ አድርግ’ ትሉኛላችሁ።
አጋንንትም “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ!” እያሉ በመጮኽ ብዙ ሰዎችን እየለቀቁ ይወጡ ነበር፤ እርሱ መሲሕ መሆኑንም ዐውቀው ነበር፤ ኢየሱስ ግን ስለ እርሱ ምንም እንዳይናገሩ በመገሠጽ ይከለክላቸው ነበር።
ደቀ መዛሙርቱ “መምህር ሆይ! መምህር ሆይ! ልናልቅ ነው!” ሲሉ ኢየሱስን ቀሰቀሱት። እርሱም ነቅቶ ነፋሱንና የሚያናውጠውን ማዕበል ገሠጻቸው፤ ነፋሱና የሚያናውጠው ማዕበል ወዲያውኑ ቆሙ፤ ታላቅ ጸጥታም ሆነ።
እነሆ! ርኩስ መንፈስ በድንገት ይዞ ያስጮኸዋል፤ በመሬት ላይ ጥሎ ዐረፋ እያስደፈቀ ያንፈራግጠዋል፤ ሰውነቱንም እያቈሰለ በአሳር ይለቀዋል።
ስለዚህ ሰማያትና በውስጣቸው የምትኖሩ ሁሉ ደስ ይበላችሁ! ጥቂት ጊዜ ብቻ እንደ ቀረው ስላወቀ ዲያብሎስ በታላቅ ቊጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና ምድርና ባሕር ወዮላችሁ!”