ነገር ግን በዐይናቸው እያዩት ማን እንደ ሆነ ማወቅ አልቻሉም።
ነገር ግን እንዳያውቁት ዐይናቸው ተይዞ ነበር።
እንዳያውቁትም ዐይናቸው ተይዞ ነበር።
ነገር ግን እንዳያውቁት ዓይናቸው ተይዞ ነበር።
ዮሴፍ ወንድሞቹን ያወቃቸው ቢሆንም እንኳ እነርሱ አላወቁትም ነበር፤
ከዚያም በኋላ ወደ ገጠር ይሄዱ ለነበሩ ሁለት ደቀ መዛሙርት ኢየሱስ በሌላ መልክ ታያቸው።
ይህንንም በሚያወሩበትና በሚወያዩበት ጊዜ ኢየሱስ ራሱ ወደ እነርሱ ቀርቦ አብሮአቸው ይጓዝ ጀመር።
እርሱም “በጒዞ ላይ ሳላችሁ የምትነጋገሩበት ይህ ነገር ምንድን ነው?” አላቸው። እነርሱም እያዘኑ ቀጥ ብለው ቆሙ።
በዚያን ጊዜ ዐይናቸው ተከፈተና ኢየሱስ መሆኑን ዐወቁ፤ እርሱ ግን ወዲያው ከዐይናቸው ተሰወረ።
ይህንንም ብላ ወደ ኋላዋ ዘወር ስትል ኢየሱስን ቆሞ አየችው፤ ኢየሱስ መሆኑን ግን አላወቀችም።
ሲነጋ ኢየሱስ በባሕሩ ዳር ቆመ፤ ደቀ መዛሙርቱ ግን ኢየሱስ መሆኑን አላወቁም።