ሉቃስ 23:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡ ግን “ስቀለው! ስቀለው!” እያለ ጮኸ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱ ግን፣ “ስቀለው! ስቀለው!” እያሉ ይጮኹ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን እነርሱ “ስቀለው! ስቀለው!” እያሉ ይጮኹ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱ ግን፥ “ስቀለው! ስቀለው!” እያሉ ይጮሁ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን እነርሱ፦ ስቀለው ስቀለው እያሉ ይጮኹ ነበር። |
ጲላጦስም ሦስተኛ ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ “ይህ ሰው ያደረገው በደል ከቶ ምንድን ነው? እኔ ለሞት የሚያደርስ ምንም ነገር አላገኘሁበትም፤ ስለዚህ ገርፌ እለቀዋለሁ።”
እነርሱ ግን “አስወግደው! አስወግደው! ስቀለው!” እያሉ ጮኹ። ጲላጦስም “ንጉሣችሁን ልስቀለውን?” አላቸው። የካህናት አለቆችም “ከሮማው ንጉሠ ነገሥት በቀር ሌላ ንጉሥ የለንም!” ሲሉ መለሱለት።