በዚያን ጊዜ በመንግሥት ላይ ተነሣሥተው፥ ሰው በመግደል ወህኒ ቤት የገቡ ዐመፀኞች ነበሩ፤ ከነዚህም ዐመፀኞች አንዱ በርባን የሚባለው ሰው ነበር።
ሉቃስ 23:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በርባን በከተማ ውስጥ ብጥብጥ በማስነሣትና ሰውን በመግደል ምክንያት በወህኒ ቤት የታሰረ ሰው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በርባንም በከተማ ውስጥ የሕዝብ ዐመፅ በማነሣሣትና በነፍስ ግድያ የታሰረ ሰው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ሁከትን በከተማ አስነሥቶ ሰውን ስለ ገደለ በወኅኒ ታስሮ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያ በርባን ግን በከተማ ሁከት ያደረገና ነፍስ በመግደል የታሰረ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ሁከትን በከተማ አንሥቶ ሰውን ስለ ገደለ በወኅኒ ታስሮ ነበር። |
በዚያን ጊዜ በመንግሥት ላይ ተነሣሥተው፥ ሰው በመግደል ወህኒ ቤት የገቡ ዐመፀኞች ነበሩ፤ ከነዚህም ዐመፀኞች አንዱ በርባን የሚባለው ሰው ነበር።
እንዲህ እያሉም ይከሱት ጀመር፤ “ይህ ሰው ሕዝባችንን ሲያስት አገኘነው፤ ለሮም ንጉሠ ነገሥት ግብር እንዳይከፈል ይከለክላል፤ ደግሞ ‘እኔ ንጉሥ መሲሕ ነኝ’ እያለ ይናገራል።”