እርሱም በሰዎች ፊት እንዲህ ብሎ ይዘምራል፤ ‘እኔ ኃጢአት ሠርቻለሁ፤ የቀናውንም ነገር አጣምሜአለሁ፤ እግዚአብሔር ግን በደሌን አልቈጠረብኝም።
ሉቃስ 22:61 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ጊዜ ጌታ ኢየሱስ ዞር ብሎ ጴጥሮስን አየው፤ ጴጥሮስም “ዛሬ ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” በማለት ጌታ ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አስታወሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታም መለስ ብሎ ጴጥሮስን ተመለከተው፤ ጴጥሮስም፣ “ዛሬ ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” ብሎ ጌታ የተናገረው ቃል ትዝ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ዘወር ብሎ ጴጥሮስን ተመለከተው፤ ጴጥሮስም “ዛሬ ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ፤” ያለው የጌታ ቃል ትዝ አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችን ኢየሱስም ዘወር ብሎ ጴጥሮስን አየው፤ ጴጥሮስም፥ “ዛሬ ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” ያለውን የጌታችንን ቃል ዐሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታም ዘወር ብሎ ጴጥሮስን ተመለከተው፤ ጴጥሮስም፦ ዛሬ ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ እንዳለው የጌታ ቃል ትዝ አለው። |
እርሱም በሰዎች ፊት እንዲህ ብሎ ይዘምራል፤ ‘እኔ ኃጢአት ሠርቻለሁ፤ የቀናውንም ነገር አጣምሜአለሁ፤ እግዚአብሔር ግን በደሌን አልቈጠረብኝም።
ይህንንም የማደርገው፥ ለፈጸምሽው በደል ሁሉ ይቅርታ ሳደርግልሽ ሥራሽን በማስታወስ በድንጋጤ ዐፍረሽ ጸጥ እንድትዪ ነው፤” ይህን የተናገረ ልዑል እግዚአብሔር ነው።
“እስራኤል ሆይ! እንዴት እተውሃለሁ? እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ? በአዳማና በጸቦይም ያደረግኹትንስ፥ እንዴት አደርግብሃለሁ? ለአንተ ያለኝ ፍቅር ታላቅ ስለ ሆነ፥ ይህን ሁሉ ላደርግብህ አልፈቅድም!
ኢየሱስም “አንተ ሕይወትህን ስለ እኔ አሳልፈህ ትሰጣለህን? እውነት፥ እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ ዶሮ ከመጮሁ በፊት ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” ሲል መለሰ።
ስለዚህ እናንተ ቀድሞ በትውልዳችሁ አሕዛብ የነበራችሁ፥ አይሁድ በሰው እጅ በመገረዛቸው እየተመኩ እናንተን ያልተገረዙ እያሉ ይሰድቡአችሁ እንደ ነበር አስታውሱ።
ከምን ያኽል ከፍተኛ ቦታ ላይ መውደቅህን አስታውስ! ንስሓም ግባ! በመጀመሪያ ታደርገው የነበረውን ሥራህን አድርግ፤ ይህን ሁሉ ባታደርግ ግን ወደ አንተ እመጣለሁ፤ ንስሓም ካልገባህ መቅረዝህን ከስፍራው አነሣዋለሁ።