ሉቃስ 21:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህም አለ፦ “በእውነት እላችኋለሁ፤ ይህች ድኻ መበለት፥ ከሁሉም አብልጣ ሰጥታለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም አለ፤ “እውነት እላችኋለሁ፤ ይህች ድኻ መበለት ከሁሉም የበለጠ ጨመረች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እውነት እላችኋለሁ፤ ይህች ድኻ መበለት ከሁሉ አብልጣ አስቀምጣለች፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም አላቸው፥ “እውነት እላችኋለሁ፥ ይህቺ ድሃ መበለት ከሁሉ ይልቅ አብዝታ ለእግዚአብሔር መባ አገባች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እውነት እላችኋለሁ፥ ይህች ድሀ መበለት ከሁሉ ይልቅ አብልጣ ጣለች፤ |
“ስሙኝ እውነቱን ልንገራችሁ፤ በነቢዩ በኤልያስ ዘመን ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ዝናም ባለመዝነቡ በአገሩ ሁሉ ብርቱ ራብ ሆኖ ነበር፤ በዚያን ጊዜ በእስራኤል አገር ብዙ ባሎቻቸው የሞቱባቸው ሴቶች ነበሩ።
“በእርግጥም ሄሮድስና ጴንጤናዊ ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር በዚህች ከተማ ተሰብስበው መሲሕ ባደረግኸው በቅዱሱ አገልጋይህ በኢየሱስ ላይ ተነሡ፤