ሉቃስ 21:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ስለ ስሜ ለመመስከር መልካም አጋጣሚ ይሆንላችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም ለመመስከር ጥሩ ዕድል ይሆንላችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም ለምስክርነት ይሆንላችኋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህም በእነርሱ ላይ ምስክር ይሆንባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህም ለምስክርነት ይሆንላችኋል። |
ተቃዋሚዎቻችሁንም በምንም ነገር አትፍሩአቸው፤ ይህም ድፍረታችሁ ለእነርሱ የመጥፋታቸው ምልክት ሲሆን ለእናንተ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ የመዳኛችሁ ምልክት ነው።
ይህ ሁሉ ነገር የሚያሳየው የእግዚአብሔር ፍርድ ትክክል መሆኑንና እናንተንም መከራ ለተቀበላችሁለት መንግሥቱ ብቁ የሚያደርጋችሁ መሆኑን ነው።