ሉቃስ 20:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ገበሬዎቹ ባዩት ጊዜ እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፤ ‘ይህ ወራሹ ነው፤ ኑ እንግደለው! ርስቱም ለእኛ ይሆናል!’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ገበሬዎቹ ግን ልጁን ባዩት ጊዜ፣ ‘ይህ እኮ ወራሹ ነው፣ ኑና እንግደለው፤ በዚህም ርስቱ የእኛ ይሆናል’ እየተባባሉ ተመካከሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተከራዮቹ ግን አይተውት እርስ በርሳቸው ሲነጋገሩ ‘ወራሹ ይህ ነው፤ ርስቱ ለእኛ እንዲሆን ኑ እንግደለው፤’ አሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ገባሮቹም ባዩት ጊዜ ወራሹ ይህ ነው፤ ኑ፥ እንግደለውና ርስቱን እንውሰድ ብለው ተማከሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገበሬዎቹ ግን አይተውት እርስ በርሳቸው ሲነጋገሩ፦ ወራሹ ይህ ነው፤ ርስቱ ለእኛ እንዲሆን ኑ እንግደለው አሉ። |
የዮሐንስ ጥምቀት ከየት መጣ? ከእግዚአብሔር ነበረ ወይስ ከሰው?” እነርሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ሲሉ ተመካከሩ፤ “ ‘ከእግዚአብሔር ነው’ ብንል ‘ታዲያ ለምን አላመናችሁትም’ ይለናል፤
ስለዚህ ልጁን ከወይኑ ተክል ቦታ ወደ ውጪ አውጥተው ገደሉት። ታዲያ፥ እንግዲህ የወይኑ ተክል ጌታ በእነዚህ ገበሬዎች ላይ ምን የሚያደርግ ይመስላችኋል?
የሕግ መምህራንና የካህናት አለቆች ይህን ምሳሌ በእነርሱ ላይ እንደ ተናገረ ዐውቀው በዚያን ሰዓት ሊይዙት ፈልገው ነበር፤ ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩ።
እርሱም ራሱ እግዚአብሔር አስቀድሞ ባቀደውና ባወቀው አሠራር መሠረት ለእናንተ ተላልፎ ተሰጠ፤ እናንተም በዐመፀኞች እጅ እንዲሰቀልና እንዲሞት አደረጋችሁት።
እንግዲህ የእግዚአብሔር ልጆች ከሆንን የእርሱ ወራሾች ነን፤ ከክርስቶስም ጋር እንወርሳለን፤ አሁን የክርስቶስ መከራ ተካፋዮች ብንሆን በኋላ የክብሩ ተካፋዮች እንሆናለን።
አሁን ግን በእነዚህ በኋለኞቹ ዘመናት ሁሉን ነገር ወራሽ ባደረገው በልጁ አማካይነት ለእኛ ተናገረን፤ ዓለምንም ሁሉ የፈጠረው በእርሱ ነው።