Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሉቃስ 22:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን ሕዝቡን ስለ ፈሩ ኢየሱስን ይዘው የሚገድሉበትን ዘዴ በስውር ይፈልጉ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 የካህናት አለቆችና ጸሐፍትም ሕዝቡን ይፈሩ ስለ ነበር፣ እንዴት አድርገው ኢየሱስን እንደሚያስወግዱት መንገድ ይፈልጉ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 የካህናት አለቆችና ጻፎች እርሱን የሚገድሉበትን መንገድ ይፈልጉ ነበር፤ ሕዝቡን ይፈሩ ነበርና።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ጻፎ​ችም ሊገ​ድ​ሉት ይሹ ነበር፤ ነገር ግን ሕዝ​ቡን ይፈ​ሩ​አ​ቸው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 የካህናት አለቆችና ጻፎችም እንዴት እንዲያጠፉት ይፈልጉ ነበር፤ ሕዝቡን ይፈሩ ነበርና።

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 22:2
12 Referencias Cruzadas  

ፈሪሳውያን ግን ከዚያ ወጥተው ኢየሱስን እንዴት አድርገው እንደሚገድሉት ተማከሩ።


ገበሬዎቹ ግን ልጁን ባዩ ጊዜ ‘ይህማ ወራሹ ነው፤ ኑ እንግደለውና ርስቱን እኛ እንውረስ!’ ተባባሉ።


“ከሁለት ቀን በኋላ የፋሲካ በዓል እንደሚሆን ታውቃላችሁ፤ የሰው ልጅ ለመሰቀል ተላልፎ ይሰጣል።”


የአይሁድ የፋሲካና የቂጣ በዓል ሊከበር ሁለት ቀን ቀርቶት ነበር፤ የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን ኢየሱስን በተንኰል ይዘው የሚገድሉበትን ዘዴ ይፈልጉ ነበር።


የሕግ መምህራንና የካህናት አለቆች ይህን ምሳሌ በእነርሱ ላይ እንደ ተናገረ ዐውቀው በዚያን ሰዓት ሊይዙት ፈልገው ነበር፤ ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩ።


ደግሞም የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ኢየሱስን መያዝ እንዲችሉ ያለበትን ቦታ የሚያውቅ ሰው ቢኖር እንዲጠቊማቸው ሰውን ሁሉ አዘው ነበር።


“በእርግጥም ሄሮድስና ጴንጤናዊ ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር በዚህች ከተማ ተሰብስበው መሲሕ ባደረግኸው በቅዱሱ አገልጋይህ በኢየሱስ ላይ ተነሡ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos