ደግ ሰው በቅንነት መንፈስ ሊቀጣኝና ሊገሥጸኝ ይችላል፤ ከክፉ ሰዎች ግን ክብርን እንኳ አልቀበልም፤ ዘወትርም ክፉ ሥራቸውን በመቃወም እጸልያለሁ።
ሉቃስ 17:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ! ወንድምህ ቢበድልህ ገሥጸው! በበደሉ ከተጸጸተም ይቅር በለው! አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። “ወንድምህ ቢበድል ገሥጸው፤ ቢጸጸት ይቅር በለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ወንድምህ ቢበድልህ ገሥጸው፤ ቢጸጸትም ይቅር በለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ወንድምህ አንተን ቢበድል ብቻህን ምከረው፤ ቢጸጸት ግን ይቅር በለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ወንድምህ ቢበድልህ ገሥጸው፥ ቢጸጸትም ይቅር በለው። |
ደግ ሰው በቅንነት መንፈስ ሊቀጣኝና ሊገሥጸኝ ይችላል፤ ከክፉ ሰዎች ግን ክብርን እንኳ አልቀበልም፤ ዘወትርም ክፉ ሥራቸውን በመቃወም እጸልያለሁ።
በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ ወደ ኢየሱስ ቀርቦ፦ “ጌታ ሆይ! ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ይቅር ልበለው? እስከ ሰባት ጊዜ ነውን?” ሲል ጠየቀው።
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “በመብልና በመጠጥ ብዛት በስካርም በመባከንና ስለ ዓለማዊ ኑሮ በመጨነቅ ልባችሁ እንዳይዝል ተጠንቀቁ! አለበለዚያ ያ ቀን እንደ ወጥመድ በድንገት ይይዛችኋል።
ስለዚህ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን እንዳትረሱ እርግጠኞች ሁኑ፤ ምንም ዐይነት የተቀረጸ ምስል እንዳትሠሩ፤ የነገራችሁንም ትእዛዝ ፈጽሙ።
እንግዲህ በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ ይህን በዐይናችሁ ያያችሁትን ሁሉ እንዳትረሱና ከአእምሮአችሁ እንዳይጠፋ ተጠንቀቁ። ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁም አስተምሩአቸው፤
ከእናንተ ማንም የእግዚአብሔር ጸጋ እንዳይጐድልበት ተጠንቀቁ፤ እንዲሁም ምንም መራራ ፍሬ የሚያፈራ ሥር በመካከላችሁ እንዳይበቅልና እንዳያስቸግራችሁ ብዙዎችንም እንዳያረክስ ተጠንቀቁ።