ጌታ ሆይ! ተመልከት! ከአሁን ቀደም እንደዚህ የጨከንክበት ሕዝብ አለ ወይ? ሴቶች የወለዱአቸውንና ያሳደጓቸውን ሕፃናት ይብሉን! በጌታ ቤተ መቅደስ ውስጥስ ካህናትና ነቢያት ይገደሉን!
ሉቃስ 13:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ ሰዎች ወደ ኢየሱስ መጥተው፥ “የገሊላ ሰዎች መሥዋዕት በሚያቀርቡበት ጊዜ ጲላጦስ ገደላቸው፤ ደማቸውም ከመሥዋዕታቸው ጋር አደባለቀ” ሲሉ ነገሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ መጥተው፣ ጲላጦስ ደማቸውን ከመሥዋዕታቸው ጋራ ስለ ደባለቀው ስለ ገሊላ ሰዎች ያወሩለት ሰዎች በዚያ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜም ሰዎች መጥተው ጲላጦስ ደማቸውን ከመሥዋዕታቸው ጋር ስላደባለቀው ስለ ገሊላ ሰዎች አወሩለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያ ወራትም ሰዎች ወደ እርሱ መጥተው ጲላጦስ ደማቸውን ከመሥዋዕታቸው ጋር ስለ ቀላቀለው ስለ ገሊላ ሰዎች ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜም ሰዎች መጥተው ጲላጦስ ደማቸውን ከመሥዋዕታቸው ጋር ስላደባለቀው ስለ ገሊላ ሰዎች አወሩለት። |
ጌታ ሆይ! ተመልከት! ከአሁን ቀደም እንደዚህ የጨከንክበት ሕዝብ አለ ወይ? ሴቶች የወለዱአቸውንና ያሳደጓቸውን ሕፃናት ይብሉን! በጌታ ቤተ መቅደስ ውስጥስ ካህናትና ነቢያት ይገደሉን!
“እናንተ የገሊላ ሰዎች፥ ስለምን ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ቆማችኋል? ይህ ወደ ሰማይ ሲያርግ ያያችሁት ኢየሱስ፥ ወደ ሰማይ ሲያርግ ባያችሁት ዐይነት ተመልሶ ይመጣል” አሉአቸው።
ከዚያም በኋላ የሕዝብ ቈጠራ በተደረገበት ዘመን ገሊላዊው ይሁዳ ተነሥቶ ብዙ ሰዎች እንዲከተሉት አድርጎ ነበር፤ እርሱም ተገደለ፤ የተከተሉትም ሁሉ ተበታተኑ።