እግዚአብሔር ሆይ! የሕይወታቸው ድርሻ የዚህ ዓለም ነገር ብቻ ከሆነ ሰዎች በእጅህ አድነኝ፤ ለምትወዳቸው ምግብን ስጣቸው፤ ልጆቻቸው ብዙ ይኑራቸው፤ የልጅ ልጆቻቸውም የተትረፈረፈ ምግብ እንዲኖራቸው አድርግ።
ሉቃስ 12:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህም አለ፦ ‘የማደርገው ይህ ነው፤ ጐተራዎቼን ሁሉ አፈርስና ሌሎች ትልልቅ ጐተራዎች እሠራለሁ፤ በዚያ እህሌንና ንብረቴን ሁሉ ሰብስቤ አከማቻለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እንዲህም አለ፤ ‘እንደዚህ አደርጋለሁ፤ ያሉኝን ጐተራዎች አፈርስና ሌሎች ሰፋ ያሉ ጐተራዎች እሠራለሁ፤ በዚያም ምርቴንና ንብረቴንም ሁሉ አከማቻለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘እንዲህ አደርጋለሁ፤ ጎተራዬን አፍርሼ ሌላ የሚበልጥ እሠራለሁ፤ በዚያም ፍሬዬንና በረከቴን ሁሉ አከማቻለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም አለ፦ እንዲህ አደርጋለሁ፤ የቀድሞውን ጎተራዬን አፈርሳለሁ፤ ከእርሱ የሚበልጥ ሌላ ጎተራም እሠራለሁ፤ እህሌንና በረከቴንም በዚያ እሰበስባለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህ አደርጋለሁ፤ ጐተራዬን አፍርሼ ሌላ የሚበልጥ እሠራለሁ፥ በዚያም ፍሬዬንና በረከቴን ሁሉ አከማቻለሁ፤ |
እግዚአብሔር ሆይ! የሕይወታቸው ድርሻ የዚህ ዓለም ነገር ብቻ ከሆነ ሰዎች በእጅህ አድነኝ፤ ለምትወዳቸው ምግብን ስጣቸው፤ ልጆቻቸው ብዙ ይኑራቸው፤ የልጅ ልጆቻቸውም የተትረፈረፈ ምግብ እንዲኖራቸው አድርግ።
እስቲ በሰማይ ላይ ወደሚበሩት ወፎች ተመልከቱ፤ እነርሱ አይዘሩም፤ አያጭዱም፤ በጐተራ አይከቱም፤ ነገር ግን የሰማዩ አባታችሁ ይመግባቸዋል። ታዲያ እናንተ ከወፎች እጅግ ትበልጡ የለምን?
ከዚህም በኋላ ራሴን፦ እነሆ፥ ለብዙ ዓመት የሚበቃህ ብዙ ሀብት አለህ፤ እንግዲህ ዕረፍት በማድረግ ተዝናና! ብላ! ጠጣ! ደስ ይበልህ! እለዋለሁ’ አለ።
እስቲ ቊራዎችን ተመልከቱ! እነርሱ አይዘሩም ወይም አያጭዱም፤ የእህል ማከማቻ ቦታ ወይም ጐተራ የላቸውም፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ይመግባቸዋል፤ እናንተማ ከወፎች የቱን ያኽል ትበልጣላችሁ!