Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሉቃስ 12:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ‘እንዲህ አደርጋለሁ፤ ጎተራዬን አፍርሼ ሌላ የሚበልጥ እሠራለሁ፤ በዚያም ፍሬዬንና በረከቴን ሁሉ አከማቻለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 “እንዲህም አለ፤ ‘እንደዚህ አደርጋለሁ፤ ያሉኝን ጐተራዎች አፈርስና ሌሎች ሰፋ ያሉ ጐተራዎች እሠራለሁ፤ በዚያም ምርቴንና ንብረቴንም ሁሉ አከማቻለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እንዲህም አለ፦ ‘የማደርገው ይህ ነው፤ ጐተራዎቼን ሁሉ አፈርስና ሌሎች ትልልቅ ጐተራዎች እሠራለሁ፤ በዚያ እህሌንና ንብረቴን ሁሉ ሰብስቤ አከማቻለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እር​ሱም አለ፦ እን​ዲህ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የቀ​ድ​ሞ​ውን ጎተ​ራ​ዬን አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ ከእ​ርሱ የሚ​በ​ልጥ ሌላ ጎተ​ራም እሠ​ራ​ለሁ፤ እህ​ሌ​ንና በረ​ከ​ቴ​ንም በዚያ እሰ​በ​ስ​ባ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እንዲህ አደርጋለሁ፤ ጐተራዬን አፍርሼ ሌላ የሚበልጥ እሠራለሁ፥ በዚያም ፍሬዬንና በረከቴን ሁሉ አከማቻለሁ፤

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 12:18
11 Referencias Cruzadas  

እንዲህ ያለችዋ ጥበብ ከላይ አይደለችም፤ ነገር ግን ምድራዊ፥ ሥጋዊና አጋንንታዊ ናት።


ይልቁንም፥ “የጌታ ፈቃድ ቢሆን እንኖራለን፤ ይህን ወይም ያንን እናደርጋለን” ማለት ይገባችኋል።


ጌታም አለ፦ “ዐመፀኛው ዳኛ ያለውን ስሙ።


ለራሱ ገንዘብ የሚያከማች፥ በእግዚአብሔር ዘንድም ባለ ጠጋ ያልሆነ እንዲህ ነው።”


ለአያሌ ቀናትም ሊፈርድላት አልፈለገም ነበር፤ ከዚህ በኋላ ግን በልቡ ‘ምንም እግዚአብሔርን ባልፈራ ሰውንም ባላፍር፥


አቤቱ፥ ከሰዎች፥ እድል ፈንታቸው በሕይወታቸው ከሆነች ከዚህ ዓለም ሰዎች በእጅህ አድነኝ፥ ከሰወርኸው መዝገብህ ሆዳቸውን አጠገብህ፥ ልጆቻቸው ተትረፍርፎላቸዋል የተረፋቸውንም ለሕፃናቶቻቸው ያተርፋሉ።


ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም፥ ወይም አያጭዱም፥ ወደ ጎተራም አይሰበስቡም፤ ነገር ግን የሰማዩ አባታችሁ ይመግባቸዋል፤ ታዲያ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?


እርሱም ‘ፍሬዬን የማከማችበት ስፍራ አጥቻለሁና ምን ላድርግ?’ ብሎ በልቡ አሰበ።


ነፍሴንም አንቺ ነፍሴ! ለብዙ ዘመን የሚቀር ብዙ በረከት አለሽ፤ ዕረፊ፤ ብዪ፤ ጠጪ፤ ደስ ይበልሽ እላታለሁ፤’ አለ።


ቁራዎችን ተመልከቱ፤ አይዘሩም፤ አያጭዱምም፤ ዕቃ ቤትም ወይም ጎተራ የላቸውም፤ እግዚአብሔርም ይመግባቸዋል፤ እናንተማ ከወፎች እጅግ ትበልጡ የለምን?


እናንተ “ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህች ወይም ወደዚያች ከተማ እንሄዳለን፤ በእርሷም አንድ ዓመት እንቈያለን፤ እንነግዳለን፤ እናተርፋለንም” የምትሉ ተመልከቱ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios