ሉቃስ 1:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናል፤ የወይን ጠጅና ሌላም የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ ገና በእናቱ ማሕፀን ሳለ በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና። የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ በእናቱም ማሕፀን ሳለ በመንፈስ ቅዱስ ይሞላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና፥ የወይን ጠጅም ሆነ የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ ገናም በእናቱ ማኅፀን ሳለ በመንፈስ ቅዱስ ይሞላል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ይሆናልና የወይን ጠጅና የሚያሰክርም መጠጥ ሁሉ አይጠጣም፤ ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮም መንፈስ ቅዱስ ይመላበታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና፥ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ ገናም በእናቱ ማኅፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ይሞላበታል፤ |
አባቱ ግን “ዐውቄአለሁ፤ ልጄ ዐውቄአለሁ፤ የምናሴም ዘር ታላቅ ሕዝብ ይሆናል፤ ይሁን እንጂ የእርሱ ታናሽ ወንድም ከእርሱ ይበልጥ ታላቅ ይሆናል፤ ዘሮቹም ታላላቅ ሕዝቦች ይሆናሉ” አለ።
በሄድክበት ስፍራ ሁሉ ከአንተ ጋር ነበርኩ፤ ጠላቶችህን ሁሉ ድል አደረግኹልህ፤ በዓለም ላይ እንዳሉት እንደታላላቅ ዝነኞች ሰዎች ስምህን ዝነኛ አደርገዋለሁ።
ብልጽግናና ክብር ሁሉ የሚገኘው ከአንተ ነው፤ አንተ ሁሉን ትገዛለህ፤ ኀይልና ብርታት ያንተ ናቸው፤ የወደድከውንም ታላቅና ብርቱ ማድረግ ይቻልሃል።
“ኤርምያስ ሆይ! ገና በእናትህ ማሕፀን እንድትፀነስ ከማድረጌ በፊት ዐውቄሃለሁ፤ ከመወለድህም በፊት አንተን በመለየት ለሕዝቦች ነቢይ አድርጌ ሾሜሃለሁ።”
እነርሱ ግን እንዲህ ሲሉ መለሱልኝ፦ “እኛ የወይን ጠጅ አንጠጣም፤ የሬካብ ልጅ የነበረው አባታችን ኢዮናዳብ እኛም ሆንን ዘሮቻችን ሁሉ ምንም ዐይነት የወይን ጠጅ እንዳንጠጣ አዞናል።
“አንተና ልጆችህ የወይን ጠጅ ወይም ሌላ የሚያሰክር መጠጥ ጠጥታችሁ ወደ መገናኛው ድንኳን እንዳትገቡ ተጠንቀቁ፤ ይህን ብታደርጉ ትሞታላችሁ፤ ይህም ሕግ ከእናንተ በኋላ በሚነሣውም ትውልድ ዘንድ ሁሉ ተጠብቆ መኖር አለበት።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይከላከልላቸዋል፤ እነርሱም ጠላቶቻቸውን ይደመስሳሉ፤ የጠላትንም የወንጭፍ ድንጋይ ይረጋግጣሉ፤ የወይን ጠጅ ጠጥቶ እንደ ሰከረ ሰው ይጮኻሉ፤ የጠላቶቻቸውም ደም የመሥዋዕት ደም በሳሕን ሞልቶ በመሠዊያ ላይ እንደሚፈስስ ይፈስሳል።
እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለው፦ “ከሙሴ ጋር እንደ ነበርኩ ከአንተም ጋር የምሆን መሆኔን ያውቁ ዘንድ እኔ ዛሬ በእስራኤላውያን ሁሉ ፊት አንተን ከፍ፥ ከፍ ማድረግ እጀምራለሁ።
በዚያን ቀን እግዚአብሔር ኢያሱን በእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አደረገው፤ ሙሴን ያከብሩት እንደ ነበር ኢያሱንም በሕይወቱ ዘመን ሁሉ አከበሩት።