አሮንም “ስለ ኃጢአት ስርየት የቀረበውን መሥዋዕት ዛሬ በልቼው ቢሆን ኖሮ ለካ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኝ ኖሮአልን? እነሆ ሕዝቡ ዛሬ ስለ ኃጢአት ስርየት የሚቀርበውን መሥዋዕትና የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አምጥተዋል፤ ነገር ግን እነዚህ እንደዚህ ያሉ ነገሮች በእኔ ላይ ደረሱ” ሲል መለሰ፤
ዘሌዋውያን 9:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሮንም ወደ መሠዊያው ሄዶ መጀመሪያ ስለ ራሱ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርበውን ጥጃ ዐረደ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሮንም ወደ መሠዊያው መጥቶ ስለ ራሱ የኀጢአት መሥዋዕት የቀረበውን እንቦሳ ዐረደው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሮንም ወደ መሠዊያው ቀርቦ ስለ ራሱ ኃጢአት መሥዋዕት የሆነውን እምቦሳ አረደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሮንም ወደ መሠዊያው ቀርቦ ስለ ራሱ ኀጢአት መሥዋዕት የሆነውን ጥጃ አረደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሮንም ወደ መሠዊያው ቀርቦ ስለ ራሱ ኃጢአት መሥዋዕት የሆነውን እምቦሳ አረደ። |
አሮንም “ስለ ኃጢአት ስርየት የቀረበውን መሥዋዕት ዛሬ በልቼው ቢሆን ኖሮ ለካ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኝ ኖሮአልን? እነሆ ሕዝቡ ዛሬ ስለ ኃጢአት ስርየት የሚቀርበውን መሥዋዕትና የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አምጥተዋል፤ ነገር ግን እነዚህ እንደዚህ ያሉ ነገሮች በእኔ ላይ ደረሱ” ሲል መለሰ፤