ዘሌዋውያን 7:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዘይት የተለወሰም ቢሆን ወይም ደረቅ ያልበሰለው የእህል መባ ግን ትውልዳቸው ከአሮን ወገን ለሆነው ካህናት ሁሉ ይሰጥ፤ እርሱንም እኩል ይካፈሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማንኛውም በዘይት የተለወሰ ወይም ደረቅ የእህል ቍርባን ለአሮን ልጆች ሁሉ እኩል ይሰጥ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዘይትም የተለወሰው ወይም የደረቀው የእህል ቁርባን በጠቅላላ ለአሮን ልጆች ሁሉ ይሆናል፤ እያንዳንዱም እንደሌላው ወንድሙ ይደርሰዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዘይትም የተለወሰው ወይም የደረቀው የእህል ቍርባን ሁሉ ለአሮን ልጆች ሁሉ ይሆናል፤ ለእያንዳንዱም እኩል ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዘይትም የተለወሰው ወይም የደረቀው የእህል ቍርባን ሁሉ ለአሮን ልጆች ሁሉ ይሆናል፤ ለሁሉም ይሆናል። |
እናንተ በምትቸገሩበት ጊዜ የእነርሱ ሀብት ለእናንተ ችግር እንዲውል አሁን የእናንተ ሀብት ለእነርሱ ችግር ይዋል፤ በዚህ ዐይነት በመካከላችሁ እኩልነት ይኖራል።