እርሱም በሰዎች ፊት እንዲህ ብሎ ይዘምራል፤ ‘እኔ ኃጢአት ሠርቻለሁ፤ የቀናውንም ነገር አጣምሜአለሁ፤ እግዚአብሔር ግን በደሌን አልቈጠረብኝም።
ዘሌዋውያን 5:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ሰው ከእነዚህ ነገሮች በአንዲቱ በደለኛ ቢሆን የሠራውን ኃጢአት ይናዘዝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማንኛውም ሰው ከእነዚህ በአንዱ በደለኛ ሆኖ ቢገኝ፣ የትኛውን ኀጢአት እንደ ሠራ ገልጾ መናዘዝ አለበት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንድ ሰው ከእነዚህ ነገሮች በአንዱ በደለኛ ቢሆን፥ የሠራውን ኃጢአት ይናዘዛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነዚህ ነገሮች በአንዲቱ በደለኛ ቢሆን፥ የሠራውን ኀጢአት ይናዘዛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነዚህ ነገሮች በአንዲቱ በደለኛ ሲሆን፥ የሠራውን ኃጢአት ይናዘዛል። |
እርሱም በሰዎች ፊት እንዲህ ብሎ ይዘምራል፤ ‘እኔ ኃጢአት ሠርቻለሁ፤ የቀናውንም ነገር አጣምሜአለሁ፤ እግዚአብሔር ግን በደሌን አልቈጠረብኝም።
በዚያን ጊዜ ኃጢአቴን ለአንተ ተናዘዝኩ፤ በደሌንም ከአንተ አልሰወርኩም፤ ኃጢአቴን ሁሉ ለአንተ ለመናዘዝ ወሰንኩ፤ አንተም ኃጢአቴን ሁሉ ይቅር አልክልኝ።
አንቺ በደለኛ መሆንሽንና በአምላክሽ በእግዚአብሔር ላይ ማመፅሽን ብቻ እመኚ፤ ከባዕዳን አማልክት ጋር በየለምለሙ ዛፍ ሥር የጣዖት አምልኮ ርኲሰት መፈጸምሽንና ለሕጌም ያለመታዘዝሽን ተናዘዢ፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር በመናዘዝ እንዲህ ስል ጸለይኩ፦ “ለሚወዱህና ትእዛዞችህን ለሚጠብቁ ቃል ኪዳንህንና ዘለዓለማዊ ፍቅርህን የምትጠብቅ ታላቅና መፈራት የሚገባህ አንተ ጌታ እግዚአብሔር ነህ።
ሁለት እጆቹን በፍየሉ ራስ ላይ ይጭናል፤ የሕዝቡን ክፋት፥ ኃጢአትና ዐመፅ ሁሉ በመናዘዝ አዛውሮ በፍየሉ ራስ ላይ ያሸክመዋል፤ ከዚህ በኋላ ለዚህ ሥራ የተመደበ ሰው ፍየሉን ነድቶ ወደ በረሓ ይወስደዋል።
ካህኑም በዚህ ዐይነት ስለዚያ ሰው ኃጢአት ማስተስረያ መሥዋዕትን ያቀርባል፤ ያም ሰው ኃጢአቱ ይቅር ይባልለታል፤ የቀረው ዱቄት የእህል መባ በሚቀርብበት ዐይነት ለካህኑ ይሁን።”