ዘሌዋውያን 4:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑም የእንስሳይቱን ደም በጣቱ እያጠቀሰ በሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያው አራት ማእዘን በሚገኙ ጒጦች ላይ ያኑር፤ ከዚህም የተረፈውን ደም በመሠዊያው ሥር ያፍስሰው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑም ከኀጢአት መሥዋዕቱ ደም በጣቱ ጥቂት ወስዶ የሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርብበትን መሠዊያ ቀንዶች ይቅባ፤ የተረፈውንም ደም ሁሉ በመሠዊያ ግርጌ ያፍስሰው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑም ከኃጢአት መሥዋዕት ደም በጣቱ ወስዶ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ ቀንዶች ላይ ያደርገዋል፥ የተረፈውንም ደምዋን ሁሉ ከመሠዊያው በታች ያፈስሳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም ከኀጢአት መሥዋዕት ደም በጣቱ ወስዶ ለሚቃጠል መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ቀንዶች ላይ ያደርገዋል፤ ደሙንም ሁሉ ከመሠዊያው በታች ያፈስሰዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም ከኃጢአት መሥዋዕት ደም በጣቱ ወስዶ ለሚቃጠል መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ቀንዶች ላይ ያደርገዋል፥ ደሙንም ሁሉ ከመሠዊያው በታች ያፈስሰዋል። |
ደግሞም ጥቂት ደም ወስዶ በድንኳኑ በእግዚአብሔር ድንኳን ፊት ባለው በመሠዊያው ጒጦች ላይ ያኑር፤ ከዚያም የተረፈውን ደም በድንኳኑ መግቢያ በኩል የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ ሥር ያፍስሰው።
ካህኑ የእንስሳውን ደም በጣቱ እያጠቀሰ በሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያው አራት ማእዘን ላይ በሚገኙ ጒጦች ላይ ያኑር፤ ከዚህ የተረፈውንም በሚቃጠል መሥዋዕት በመሠዊያው ሥር ያፍስሰው።
ካህኑም የእንስሳይቱን ደም በጣቱ እያጠቀሰ በሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያው አራት ማእዘን በሚገኙ ጒጦች ላይ ያኑር፤ ከዚህም የተረፈውን ደም በመሠዊያው ሥር ያፍስሰው።
ከዚያም ደግሞ ጥቂት ደም ወስዶ በድንኳኑ ውስጥ በዕጣን መሠዊያው አራት ማእዘን ጒጦች ላይ ያኑር፤ የተረፈውን ደም ግን በድንኳኑ መግቢያ በኩል የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ ሥር ያፍስሰው።
ከሰው ባሕርይ ደካማነት የተነሣ ሕግ ሊያደርገው ያልቻለውን እግዚአብሔር አድርጎታል፤ የገዛ ልጁንም በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌነት በኃጢአት ምክንያት ልኮ በሥጋው ኃጢአትን በፍርድ አስወገደ።
ታዲያ፥ የእግዚአብሔርን ልጅ የናቀ፥ የተቀደሰበትን የቃል ኪዳን ደም ያረከሰ፥ የጸጋን መንፈስ የሰደበ፥ እንዴት ያለ የባሰ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል!
ሁሉ ነገር በእርሱና ለእርሱ የተፈጠረው እግዚአብሔር ብዙ ልጆችን ወደ ክብር ለማምጣት የመዳናቸውን መሪ ኢየሱስን በመከራ ፍጹም እንዲሆን እንዲያደርገው ተገባው።
ክርስቶስም ራሱ ወደ እግዚአብሔር ያቀርበን ዘንድ እርሱ ጻድቅ ሆኖ ሳለ ጽድቅ ለሌለን ለእኛ በኃጢአታችን ምክንያት በማያዳግም ሁኔታ አንድ ጊዜ መከራን በመቀበል ሞቶአል፤ እርሱ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ።