የቄዳር የበግ መንጋዎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባሉ፤ የነባዮት አውራ በጎችም ለመሥዋዕትነት ያገለግሉሻል፤ በመሠዊያም ላይ ለመሥዋዕትነት ለመቅረብ ተቀባይነት ይኖራቸዋል። የተከበረውን ቤተ መቅደሴንም አስጌጣለሁ።
ዘሌዋውያን 3:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ አንድነት የሚቀርበው መሥዋዕት በግ ቢሆን፥ ተባዕትም ሆነ እንስት ምንም ነውር የማይገኝበት ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ከበግ ወይም ከፍየሉ መንጋ ለእግዚአብሔር የኅብረት መሥዋዕት የሚያቀርብ ከሆነ፣ እንከን የሌለበትን ተባዕት ወይም እንስት ያቅርብ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለጌታም ለአንድነት መሥዋዕት የሚያቀርበው ቁርባኑ ከበጎች ተባት ወይም እንስት ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ያቀርባል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለእግዚአብሔርም ለደኅንነት መሥዋዕት የሚያቀርበው ቍርባኑ ከበጎች ተባት ወይም እንስት ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ያቀርባል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእግዚአብሔርም ለደኅንነት መሥዋዕት የሚያቀርበው ቍርባኑ ከበጎች ተባት ወይም እንስት ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ያቀርባል። |
የቄዳር የበግ መንጋዎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባሉ፤ የነባዮት አውራ በጎችም ለመሥዋዕትነት ያገለግሉሻል፤ በመሠዊያም ላይ ለመሥዋዕትነት ለመቅረብ ተቀባይነት ይኖራቸዋል። የተከበረውን ቤተ መቅደሴንም አስጌጣለሁ።
እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር መባ በሚያቀርቡበት ጊዜ ሊጠብቁት የሚገባ ሥርዓት ይህ ነው፦ እያንዳንዱ ሰው ከቀንድ ከብትም ሆነ፥ ከበግ ወይም ከፍየል ወገን ማንኛውንም ዐይነት መባ በሚያቀርብበት ጊዜ፥
ከዚያም ቀጥሎ ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት አንድ ተባዕት ፍየል፤ ለአንድነት መሥዋዕት የአንድ ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሁለት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ፤
እዚያ ቊርባኑን ለእግዚአብሔር ያቀርባል፤ ይኸውም ለሚቃጠል መሥዋዕት አንድ ዓመት የሞላው የበግ ጠቦት፥ ስለ ኃጢአት ስርየት ለሚቀርበውም መሥዋዕት አንድ ዓመት የሞላት አንዲት የበግ ቄብ እንዲሁም የአንድነት መሥዋዕት አንድ አውራ በግ ያቀርባል ማለት ነው።
“በእርግጥም ሄሮድስና ጴንጤናዊ ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር በዚህች ከተማ ተሰብስበው መሲሕ ባደረግኸው በቅዱሱ አገልጋይህ በኢየሱስ ላይ ተነሡ፤
ጊዜው ሲደርስ እግዚአብሔር በሥራ ላይ የሚያውለው ዕቅድ በሰማይና በምድር ያሉት ፍጥረቶች ሁሉ ተጠቃለው በአንዱ በክርስቶስ ሥልጣን ሥር እንዲሆኑ ነው።