ቀድሞ ያልተነገራቸውን ነገር ስለሚያዩና ያልሰሙትን ነገር ስለሚያስተውሉ ብዙ ሕዝቦች ስለ አገልጋዬ ይደነቃሉ፤ ነገሥታትም በእርሱ በመደነቅ የሚናገሩትን ያጣሉ።”
ዘሌዋውያን 3:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እጁንም በፍየሉ ራስ ላይ ጭኖ በድንኳኑ ፊት ለፊት ይረደው፤ ካህናቱ ደሙን ተቀብለው በመሠዊያው ዙሪያ ይርጩት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በራሱም ላይ እጁን ይጫንበት፤ በመገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት ይረደው፤ የአሮንም ልጆች ደሙን በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ይርጩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እጁንም በራሱ ላይ ይጭንበታል፥ በመገናኛውም ድንኳን ፊት ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ደሙን በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እጁንም በራሱ ላይ ይጭንበታል፤ በምስክሩ ድንኳን ደጃፍም ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ደሙን በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እጁንም በራሱ ላይ ይጭንበታል፥ በመገናኛውም ድንኳን ፊት ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ደሙን በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል። |
ቀድሞ ያልተነገራቸውን ነገር ስለሚያዩና ያልሰሙትን ነገር ስለሚያስተውሉ ብዙ ሕዝቦች ስለ አገልጋዬ ይደነቃሉ፤ ነገሥታትም በእርሱ በመደነቅ የሚናገሩትን ያጣሉ።”
ሁላችንም እንደ በጎች ባዝነን ነበር፤ ሁላችንም ወደ ራሳችን መንገድ ሄደን ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የሁላችንንም በደል በእርሱ ላይ አኖረ።
እግዚአብሔር አብ አስቀድሞ በዐቀደው መሠረት ለተመረጣችሁት፥ ለኢየሱስ ክርስቶስ ለመታዘዝና በደሙ ተረጭታችሁ ለመንጻት በመንፈስ ቅዱስ ለተቀደሳችሁት፥ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።
ክርስቶስም ራሱ ወደ እግዚአብሔር ያቀርበን ዘንድ እርሱ ጻድቅ ሆኖ ሳለ ጽድቅ ለሌለን ለእኛ በኃጢአታችን ምክንያት በማያዳግም ሁኔታ አንድ ጊዜ መከራን በመቀበል ሞቶአል፤ እርሱ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ።