ዐሞናውያንም የሶርያውያንን መሸሽ ባዩ ጊዜ እነርሱም ከአቢሳ ፊት ሸሽተው ወደ ከተማይቱ አፈገፈጉ፤ ከዚህ በኋላ ኢዮአብ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።
ዘሌዋውያን 26:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠላቶቻችሁን ታሳድዳላችሁ፤ በፊታችሁም በጦርነት ያልቃሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠላቶቻችሁን ታሳድዳላችሁ፤ እነርሱም በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠላቶቻችሁንም ታሳድዳላችሁ፥ በእናንተም ፊት በሰይፍ ይወድቃሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠላቶቻችሁንም ታሳድዳላችሁ፤ በፊታችሁም በሰይፍ ይወድቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጠላቶቻችሁንም ታሳድዳላችሁ፥ በፊታችሁም በሰይፍ ይወድቃሉ። |
ዐሞናውያንም የሶርያውያንን መሸሽ ባዩ ጊዜ እነርሱም ከአቢሳ ፊት ሸሽተው ወደ ከተማይቱ አፈገፈጉ፤ ከዚህ በኋላ ኢዮአብ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።
እንዲሁም በንጉሠ ነገሥቱ ግዛት በየሀገሩ የሚኖሩ አይሁድ ሁሉ አንድነታቸውን በማጠናከር ተደራጅተው ራሳቸውን ተከላከሉ፤ ይጠሉአቸው የነበሩትንም ሰባ አምስት ሺህ ሕዝብ በመግደል ከጠላቶቻቸው እጅ ራሳቸውን አዳኑ፤ ይሁን እንጂ ምንም ዐይነት የንብረት ዝርፊያ አላካሄዱም።
“ከስደት የቀሩት ሁሉ ነፋስ የሚነካውን የቅጠል ኮሽታ በሰሙ ቊጥር በድንጋጤ በርግገው እንዲሸሹ አደርጋለሁ፤ በጦርነት ላይ ልክ ጠላት እንደሚያሳድዳቸው ያኽል ሆነው ይሸሻሉ፤ ምንም ዐይነት ጠላት በአጠገባቸው ሳይኖር ተደናቅፈው ይወድቃሉ፤
“በምድራችሁ ሰላምን እሰጣችኋለሁ፤ ማንንም ሳትፈሩ ያለ ስጋት ትተኛላችሁ፤ አደገኞች የሆኑ አራዊትን ከምድራችሁ አስወግዳለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ጦርነት በዚያ አይኖርም።
“ጠላቶችህ በአንተ ላይ አደጋ በሚጥሉበት ጊዜ እግዚአብሔር እነርሱን ድል ያደርግልሃል፤ በአንድ አቅጣጫ ይመጡብሃል፤ ነገር ግን በሰባት አቅጣጫ ይሸሻሉ።
አምላካችሁ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ተስፋ መሠረት ስለ እናንተ ስለሚዋጋ ከእናንተ አንዱ ብቻውን ሆኖ ከእነርሱ ወገን አንዱን ሺህ ማባረር ይችላል፤
ባራቅም ሠረገሎቹንና ሠራዊቱን የአሕዛብ ይዞታ እስከ ሆነችው እስከ ሐሮሼት ድረስ አሳደዳቸው፤ የሲሣራም ሠራዊት በሙሉ በሰይፍ ተገደሉ፤ አንድ ሰው እንኳ አልተረፈም።
ዮናታንም በእጁና በጒልበቱ እየዳኸ ወደ አፋፉ ወጣ፤ ጋሻጃግሬውም ተከተለው፤ ዮናታንም በፍልስጥኤማውያን ላይ ድንገተኛ አደጋ በመጣል መታቸው፤ ጋሻጃግሬውም ገደላቸው።