ዘሌዋውያን 24:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ማንም ሰው በሌላ ሰው ላይ ጒዳት ቢያደርስ የዚያኑ ዐይነት ጒዳት ይድረስበት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማንኛውም ሰው በባልንጀራው ላይ ጕዳት ቢያደርስ፣ የዚያው ዐይነት ጕዳት ይፈጸምበት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውም ባልንጀራው ላይ ጉዳት ቢያደርስ፥ እርሱ እንዳደረገ እንዲሁ ይደረግበት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውም ባልንጀራውን ቢጎዳ፥ እርሱ እንዳደረገ እንዲሁ ይደረግበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውም ባልንጀራውን ቢጐዳ፥ እርሱ እንዳደረገ እንዲሁ ይደረግበት። |
የሌላውን ሰው አጥንት ቢሰብር አጥንቱ ይሰበር፤ የሌላውን ሰው ዐይን ቢያወጣ ዐይኑ ይውጣ፤ ጥርስም ቢሰብር ጥርሱ ይሰበር። በሌላ ሰው ላይ ምንም ዐይነት ጒዳት ቢያደርስ የዚያው ዐይነት ጒዳት በእርሱ ላይ ይመለስበት።
በእንደዚህ ያለው ክፉ ነገር ላይ ሁሉ ምንም ዐይነት ምሕረት አይኑርህ፤ የቅጣቱም አፈጻጸም ሕይወት ያጠፋ፥ ሕይወቱ እንዲጠፋ፤ ዐይን ያጠፋ፥ ዐይኑ እንዲጠፋ፤ ጥርስ ያወለቀ፥ ጥርሱ እንዲወልቅ፤ እጅ የቈረጠ፥ እጁ እንዲቈረጥ፤ እግርም የሰበረ፥ እግሩ እንዲሰበር በማድረግ ይሁን።
አዶኒቤዜቅም “የእጆቻቸውና የእግሮቻቸው አውራ ጣቶች የተቈረጡባቸው ሰባ ነገሥታት ከገበታዬ ሥር ፍርፋሪ እየለቀሙ ይበሉ ነበር፤ በእነርሱ ላይ የፈጸምኩትን ግፍ ዛሬ እግዚአብሔር በእኔ ላይ መልሶ አመጣብኝ” ሲል ተናገረ። ወደ ኢየሩሳሌምም ተወስዶ በዚያው ሞተ።