ከእህል መባውም የተረፈው ዱቄት የአሮን ዘር ለሆኑት ካህናት ይሰጥ፤ እርሱም ለእግዚአብሔር ከቀረበው መባ የሚቃጠል ቊርባን በመሆኑ እጅግ የተቀደሰ ነው።
ዘሌዋውያን 21:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአጠቃላይ ከካህኑ አሮን ዘሮች መካከል የአካል ጒድለት ያለበት ማንም ሰው የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም የምግብ ቊርባን ለአምላኩ ማቅረብ አይችልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከካህኑ ከአሮን ዘር ማንኛውም ዐይነት የአካል ጕድለት ያለበት ሰው ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት ሊያቀርብ አይምጣ፤ እንከን ያለበት ስለ ሆነ፣ የአምላኩን ምግብ ለማቅረብ አይምጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከካህኑ ከአሮን ዘር ነውር ያለበት ማናቸውም ሰው ለጌታ በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን ለማቅረብ አይቅረብ፤ ነውረኛ ነውና የአምላኩን እንጀራ ለማቅረብ አይቅረብ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከካህኑ ከአሮን ዘር ነውር ያለበት ሰው የእግዚአብሔርን መሥዋዕት ያቀርብ ዘንድ አይቅረብ፤ ነውረኛ ነው፤ የአምላኩን መባ ያቀርብ ዘንድ አይቅረብ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከካህኑ ከአሮን ዘር ነውር ያለበት ሰው የእግዚአብሔርን የእሳት ቍርባን ያቀርብ ዘንድ አይቅረብ፤ ነውረኛ ነው፤ የአምላኩን እንጀራ ያቀርብ ዘንድ አይቅረብ። |
ከእህል መባውም የተረፈው ዱቄት የአሮን ዘር ለሆኑት ካህናት ይሰጥ፤ እርሱም ለእግዚአብሔር ከቀረበው መባ የሚቃጠል ቊርባን በመሆኑ እጅግ የተቀደሰ ነው።
“ለአሮን እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘ከዘርህ የአካል ጒድለት ያለበት ማንም ሰው የእኔን የአምላኩን የምግብ መባ ማቅረብ የለበትም፤ ይህም ሥርዓት በሚመጡት ዘመናት ሁሉ ተጠብቆ ይኖራል፤
የሚቃጠል መሥዋዕትና የምግብ መባ ለእኔ ለአምላካቸው የሚያቀርቡ ካህናት ለእኔ የተለዩና ስሜንም የማያረክሱ መሆን አለባቸው፤ ስለዚህ የተቀደሱ ይሆናሉ።
ሕዝቡም ካህኑን ቅዱስ እንደ ሆነ ይቊጠረው፤ እርሱ ለእኔ ለአምላካችሁ የምግብ መባ ያቀርባል፤ እኔ የምቀድሳችሁ እኔ እግዚአብሔር ቅዱስ ነኝ፤