Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 21:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ከካ​ህኑ ከአ​ሮን ዘር ነውር ያለ​በት ሰው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ርብ ዘንድ አይ​ቅ​ረብ፤ ነው​ረኛ ነው፤ የአ​ም​ላ​ኩን መባ ያቀ​ርብ ዘንድ አይ​ቅ​ረብ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ከካህኑ ከአሮን ዘር ማንኛውም ዐይነት የአካል ጕድለት ያለበት ሰው ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት ሊያቀርብ አይምጣ፤ እንከን ያለበት ስለ ሆነ፣ የአምላኩን ምግብ ለማቅረብ አይምጣ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ከካህኑ ከአሮን ዘር ነውር ያለበት ማናቸውም ሰው ለጌታ በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን ለማቅረብ አይቅረብ፤ ነውረኛ ነውና የአምላኩን እንጀራ ለማቅረብ አይቅረብ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 በአጠቃላይ ከካህኑ አሮን ዘሮች መካከል የአካል ጒድለት ያለበት ማንም ሰው የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም የምግብ ቊርባን ለአምላኩ ማቅረብ አይችልም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ከካህኑ ከአሮን ዘር ነውር ያለበት ሰው የእግዚአብሔርን የእሳት ቍርባን ያቀርብ ዘንድ አይቅረብ፤ ነውረኛ ነው፤ የአምላኩን እንጀራ ያቀርብ ዘንድ አይቅረብ።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 21:21
4 Referencias Cruzadas  

ከመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱም የተ​ረ​ፈው ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ይሆ​ናል፤ ይህም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት የተ​ረፈ ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።


“ለአ​ሮን እን​ዲህ ብለህ ንገ​ረው፦ ከወ​ገ​ንህ በት​ው​ል​ዳ​ቸው ነውር ያለ​በት ሰው ሁሉ የአ​ም​ላ​ኩን መባ ያቀ​ርብ ዘንድ አይ​ቅ​ረብ።


ለአ​ም​ላ​ካ​ቸው ቅዱ​ሳን ይሁኑ፤ የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም ስም አያ​ር​ክሱ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውን መባ ያቀ​ር​ባ​ሉና ቅዱ​ሳን ይሁኑ።


የአ​ም​ላ​ክ​ህን መባ ያቀ​ር​ባ​ልና ስለ​ዚህ ትቀ​ድ​ሰ​ዋ​ለህ፤ እኔም የም​ቀ​ድ​ሳ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ ነኝና እርሱ ቅዱስ ይሁ​ን​ልህ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos