እስራኤል በላይኛው ቅርንጫፍ ላይ ሁለት ወይም ሦስት ፍሬዎች ብቻ እንዳሉት፥ እንዲሁም በታችኛው ቅርንጫፉ ላይ አራት ወይም አምስት ፍሬዎች እንደ ቀሩበት የወይራ ዛፍ ትሆናለች፤ ሆኖም ጥቂት ሕዝቦች ይተርፋሉ። እኔ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
ዘሌዋውያን 19:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የወይን መከርህንም ስትሰበስብ በሐረጉ ላይ ተሰውሮ የቀረውን ወይም በመሬት ላይ የረገፈውን የወይን ዘለላ አጥርተህ ለመልቀም እንደገና ወደ ኋላ አትመለስ፤ ይህን ሁሉ ለድኾችና ለመጻተኞች ተውላቸው፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የወይንህን ዕርሻ አትቃርም፤ የወደቀውንም አትልቀም፤ ለድኾችና ለመጻተኞች ተውላቸው፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወይንህንም ቃርሚያ አትቃርም፥ የወደቀውንም የወይንህን ፍሬ አትሰብስብ፤ ለድሀውና ለእንግዳው ተወው፤ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የወይንህን ቃርሚያ አጥርተህ አትቃርም፤ የወደቀውንም የወይንህን ፍሬ አትሰብስብ፤ ለድሆችና ለእንግዶች ተወው፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወይንህንም ቃርሚያ አትቃርም፥ የወደቀውንም የወይንህን ፍሬ አትሰብስብ፤ ለድሆችና ለእንግዶች ተወው፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ። |
እስራኤል በላይኛው ቅርንጫፍ ላይ ሁለት ወይም ሦስት ፍሬዎች ብቻ እንዳሉት፥ እንዲሁም በታችኛው ቅርንጫፉ ላይ አራት ወይም አምስት ፍሬዎች እንደ ቀሩበት የወይራ ዛፍ ትሆናለች፤ ሆኖም ጥቂት ሕዝቦች ይተርፋሉ። እኔ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
በዓለም መንግሥታት ሁሉ ላይ የሚደርሰው ሁኔታ ይህ ነው፤ የወይራ ፍሬ ከዛፍ ሁሉ ላይ ተለቅሞ፥ የወይንም ዘለላ ከተሰበሰበ በኋላ እንደሚታይ የመከር መጨረሻ ይሆናል።
ሰዎች የወይን ዘለላ በሚለቅሙበት ጊዜ በወይኑ ተክል ላይ ጥቂት ቃርሚያ ይተዋሉ፤ ወንበዴዎችም በሌሊት በመጡ ጊዜ የሚፈልጉትን ያኽል ብቻ ይወስዳሉ፤
እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ፤ እኔ ቅዱስ ስለ ሆንኩ እናንተም ራሳችሁን የተቀደሰ አድርጉ፤ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱትን ነፍሳት በመብላት ራሳችሁን አታርክሱ።
በአምስተኛው ዓመት ግን ፍሬውን ትበላላችሁ፤ ይህን ብታደርጉ ዛፎቻችሁ በየጊዜው የሚሰጡአችሁ ፍሬ ይበልጥ እየበዛ ይሄዳል፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።
“የምድራችሁን መከር በምትሰበስቡበት ጊዜ በእርሻችሁ ድንበር ያለውን እህል አትጨዱ፤ ስታጭዱ የቀረውንም ቃርሚያ ለመሰብሰብ ወደ ኋላ አትመለሱ፤
“የምድራችሁን መከር በምትሰበስቡበት ጊዜ የእርሻችሁን ድንበር አትጨዱ፤ የመከሩንም ቃርሚያ ለመሰብሰብ ወደ ኋላ አትመለሱ፤ እርሱን ለድኾችና ለመጻተኞች ተዉላቸው፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።”
በምድር ሰንበት ዓመት የሚበቅለው ሰብል ሁሉ ለአንተ፥ ለወንድ አገልጋይህ፥ ለሴት አገልጋይህ፥ ለቅጥረኛህ፥ ከአንተ ጋር ለሚኖር ጊዜያዊ መጻተኛ ምግብ ይሆናል።
“ሌቦች ወይም ቀማኞች በሌሊት ቢመጡ፥ የሚበቃቸውን ያኽል ብቻ ይወስዳሉ፤ የወይን ምርትንም የሚሰበስቡ ቃርሚያ ይተዋሉ፤ የአንተ ጠላቶች ግን ፈጽሞ ያጠፉሃል።
የመከር ፍሬ ተሰብስቦ የወይኑም ቃርሚያ ከተቃረመ በኋላ ሊበላ የሚፈልገውን የወይን ዘለላ እንደማያገኝ ሰው ስለ ሆንኩ ወዮልኝ! እኔ የምመኘውም አስቀድሞ የደረሰው የበለስ ፍሬ የለም።
“እህልህን በምትሰበስብበት ጊዜ የረሳኸው ነዶ ቢኖር እርሱን ለማምጣት ወደ ኋላ አትመለስ፤ እርሱ ለመጻተኞች፥ ወላጆቻቸው ለሞቱባቸው ልጆችና ባሎቻቸው ለሞቱባቸው መበለቶች ይቅርላቸው፤ ይህን ብታደርግ በምትሠራው ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ይባርክሃል።
የወይራ ዛፍ ፍሬህንም አንድ ጊዜ ከለቀምክ በኋላ የቀረውን ፍሬ ለመውሰድ እንደገና ወደ እርሱ አትመለስ፤ እርሱን ለመጻተኞች፥ ወላጆቻቸው ለሞቱባቸው ልጆችና ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች ተውላቸው።
የወይንህንም ዘለላ በምትሰበስብበት ጊዜ የቀረውን ፍሬ ለመውሰድ ወደ ወይኑ ሐረግ ዳግመኛ አትመለስ፤ የቀሩትን ዘለላዎች ለመጻተኞች፥ ወላጆቻቸው ለሞቱባቸው ልጆችና ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች ተውላቸው።
እርሱ ግን እንዲህ አላቸው፤ “እኔ ካደረግሁት እናንተ ያደረጋችኹት አይበልጥምን? የእኔ ጐሣ በሙሉ ከሠራው ሥራ የኤፍሬም ሰዎች የሠራችሁት ጥቂቱ ሥራ ይበልጣል። የኤፍሬም ወይን ቃርሚያ ከአቢዔዜር ወይን መከር አይሻልምን?
አንድ ቀን ሞአባዊትዋ ሩት ናዖሚን “በፊቱ ሞገስ ወደማገኝበት ሰው እርሻ ሄጄ ቃርሚያ ልቃርም” አለቻት። ናዖሚም “ልጄ ሆይ! ሂጂ!” አለቻት።