Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 24:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 በዓለም መንግሥታት ሁሉ ላይ የሚደርሰው ሁኔታ ይህ ነው፤ የወይራ ፍሬ ከዛፍ ሁሉ ላይ ተለቅሞ፥ የወይንም ዘለላ ከተሰበሰበ በኋላ እንደሚታይ የመከር መጨረሻ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 የወይራ ዛፍ ሲመታ፣ የወይንም ዘለላ ሲቈረጥ ቃርሚያ እንደሚቀር ሁሉ፣ በምድሪቱ ላይ፣ በሕዝቦችም ላይ እንዲሁ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 የወይራን ዛፍ እንደ መምታት፥ ከወይንም መከር በኋላ ቃርሚያውን እንደ መልቀም፥ እንዲሁ በምድርና በአሕዛብም መካከል ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ይህ ሁሉ በሀ​ገር ውስጥ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ይሆ​ናል። የወ​ይራ ፍሬ ለቀማ ባለቀ ጊዜ በቃ​ር​ሚ​ያው ውስጥ የወ​ይራ ፍሬ እን​ደ​ሚ​ለ​ቀም እን​ዲሁ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ይቃ​ር​ሟ​ቸ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 የወይራን ዛፍ እንደ መምታት፥ ከወይንም መከር በኋላ ቃርሚያውን እንደ መልቀም፥ እንዲሁ በምድር መካከል በአሕዛብም መካከል ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 24:13
19 Referencias Cruzadas  

የሠራዊት አምላክ ከጥፋት የሚተርፍ ዘር ባያስቀርልንማ ኖሮ እንደ ሰዶም በሆንን፥ እንደ ገሞራም በመሰልን ነበር።


“በዚያን ቀን የእስራኤል ታላቅነት ይዋረዳል፤ ብልጽግናቸውም ጠፍቶ ይደኸያሉ።


ገበሬ ስንዴውን ከገለባ እንደሚለይ በዚያን ቀን ከኤፍራጥስ ወንዝ አንሥቶ እስከ ግብጽ ወሰን ድረስ ያሉትን ሕዝቡን እስራኤልን እግዚአብሔር አንድ በአንድ ይሰበስባል።


ከዐሥሩ አንድ ክፍል ቢተርፍም እንኳ እርሱም እንደ ግራር ወይም እንደ ዋርካ እንደገና ይቃጠላል። ዛፉ ሲቈረጥ ጉቶው ይቀራል። ጉቶውም የተቀደሰ ዘር ነው።”


ነገር ግን ከእናንተ ጥቂቶች ብቻ ከሞት ተርፈው ከግብጽ ወደ ይሁዳ ይመለሳሉ፤ በዚያን ጊዜ ወደ ግብጽ የወረዱ ስደተኞች የእኔ ወይስ የእናንተ የማንኛችን ቃል እውነት እንደ ሆነ ያረጋግጣሉ፤


የሸለቆ ርግቦች ራሳቸውን ለማዳን ወደ ተራራ እንደሚወጡ እንዲሁም ከሰዎቹ መካከል ከሞት የተረፉ ካሉ በተራራ ላይ ተገኝተው በኃጢአታቸው ምክንያት እንደ ሸለቆ ርግቦች የሐዘን እንጒርጒሮ ያሰማሉ።


“የምድራችሁን መከር በምትሰበስቡበት ጊዜ በእርሻችሁ ድንበር ያለውን እህል አትጨዱ፤ ስታጭዱ የቀረውንም ቃርሚያ ለመሰብሰብ ወደ ኋላ አትመለሱ፤


“የእስራኤል ሕዝብ! በጎች በበረት፥ የበግ መንጋም በማሰማሪያ ቦታ እንደሚሰበሰብ በእርግጥ ከእስራኤል ሕዝብ የተረፉትን በአንድነት እሰበስባለሁ፤ ምድሪቱም በሕዝብ የተሞላች ትሆናለች” ይላል እግዚአብሔር።


የመከር ፍሬ ተሰብስቦ የወይኑም ቃርሚያ ከተቃረመ በኋላ ሊበላ የሚፈልገውን የወይን ዘለላ እንደማያገኝ ሰው ስለ ሆንኩ ወዮልኝ! እኔ የምመኘውም አስቀድሞ የደረሰው የበለስ ፍሬ የለም።


እነዚያ ቀኖች ባያጥሩማ ኖሮ አንድም ሰው መዳን ባልቻለ ነበር፤ ነገር ግን ስለ ተመረጡት ሰዎች እነዚያ ቀኖች ያጥራሉ።


ነገር ግን ልብሳቸውን ያላረከሱ በሰርዴስ ጥቂት ሰዎች ከአንተ ጋር አሉ፤ እነርሱ ነጭ ልብስ መልበስ የሚገባቸው ስለ ሆኑ ነጭ ልብስ ለብሰው ከእኔ ጋር ይሄዳሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos