ዘሌዋውያን 11:38 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን በዘሩ ላይ ውሃ ከፈሰሰበት በኋላ አንዳች በድን ቢነካው ዘሩ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን በዘሩ ላይ ውሃ ከፈሰሰበት በኋላ በድን ቢወድቅበት ዘሩ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን በዘሩ ላይ ውኃ ቢፈስበትና ከላዩም በድናቸው ቢወድቅበት፥ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን በዘሩ ላይ ውኃ ቢፈስስበት፥ ከዚህ በኋላ ከበድናቸው አንዳች ቢወድቅበት፥ ለእናንተ ርኩስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን በዘሩ ላይ ውኃ ቢፈስስበት፥ ከዚህ በኋላ ከበድናቸው አንዳች ቢወድቅበት፥ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው። |