ሰቈቃወ 5:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አባቶቻችን በጠላት እጅ ተገደሉ፤ ስለዚህ እኛ አባት የሌለን፥ እነሆ እናቶቻችንም ባል አልባ ሆነው ቀርተዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወላጅ አልባና አባት የሌላቸው ሆንን፤ እናቶቻችን እንደ መበለቶች ሆኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድሀ አደጎችና አባት የሌለን ሆነናል፥ እናቶቻችን እንደ መበለቶች ሆነዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድሀ-አደጎች ሆነናል፤ አባትም የለንም። እናቶቻችን እንደ መበለቶች ሆነዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድሀ አደጎችና አባት የሌለን ሆነናል፥ እናቶቻችን እንደ መበለቶች ሆነዋል። |
በምድራችሁ ላይ የሚገኙት ባሎቻቸው የሞቱባቸው ሴቶች ብዛታቸው ከባሕር አሸዋ የሚበልጥ ሆኖአል፤ በእኩለ ቀን በወጣቶች እናቶች ላይ ሞትን አመጣለሁ በእነርሱም ላይ ሽብርንና ጭንቀትን በቅጽበት አመጣለሁ።
አምላክ ሆይ! አሁን ግን ልጆቻቸው በራብ እንዲያልቁ፥ እነርሱም በጦርነት እንዲወድቁ አድርግ፤ ሴቶቻቸው ያለ ባልና ያለ ልጅ ይቅሩ፤ ወንዶቻቸው በበሽታ ወጣቶቻቸውም በጦርነት ይደምሰሱ።
አሦር አያድነንም፥ በጦር ፈረሶችም አንታመንም፤ ከእንግዲህ ወዲህ በእጃችን የሠራነውን ጣዖት ሁሉ ‘አምላክ’ ብለን አንጠራም፤ አምላክ ሆይ! ወላጆቻቸው የሞቱባቸው በአንተ ምሕረትን ያገኛሉ።”