Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 22:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ይህን ብታደርጉ ወደ እኔ ሲጮኹ እኔ እግዚአብሔር ጩኸታቸውን በእርግጥ እሰማለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ግፍ ብትውሉባቸውና ወደ እኔ ቢጮኹ፣ ጩኸታቸውን በርግጥ እሰማለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ቁጣዬም ይነዳል፥ በሰይፍም እገድላችኋለሁ፥ ሚስቶቻችሁ መበለት፥ ልጆቻችሁም ድሀ አደጎች ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ብታ​ስ​ጨ​ን​ቁ​አ​ቸ​ውና ወደ እኔ ቢጮኹ እኔ ጩኸ​ታ​ቸ​ውን ፈጽሞ እሰ​ማ​ለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ብታስጨንቁአቸውና ወደ እኔ ቢጮኹ እኔ ጩኸታቸውን ፈጽሞ እሰማለሁ፤

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 22:23
19 Referencias Cruzadas  

ድኾችን በመጨቈን ወደ እግዚአብሔር እንዲጮኹ አድርገዋቸዋል፤ እግዚአብሔርም የድኾችን ጩኸት ሰምቶአል።


ሰዎች ጭቈና ሲበዛባቸው ይጮኻሉ፤ ከሚበረታባቸውም እጅ የሚታደጋቸውን ለማግኘት፥ አቤቱታ ያሰማሉ።


አምላክ ሆይ! አንተ ግን ችግርንና ጭንቀትን አይተህ ልታስወግዳቸው መፍትሔ ታዘጋጃለህ፤ ችግረኛ ራሱን ለአንተ ይሰጣል፤ አንተም የሙት ልጆችን ትረዳለህ።


እግዚአብሔር ሆይ! ለድኾች እንደምትፈርድ፥ ለተጨቈኑትም መብታቸውን እንደምታስከብር ዐውቃለሁ።


በአክብሮት ለሚፈሩት የሚያስፈልጋቸውን ነገር ሁሉ ይሰጣቸዋል፤ ጩኸታቸውንም ሰምቶ ያድናቸዋል።


መከራ በደረሰብኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ እንዲረዳኝም አምላኬን ለመንኩት፤ በመቅደሱ ሆኖ ድምፄን ሰማ፤ ጩኸቴንም አደመጠ።


በተቀደሰ መኖሪያው ያለ አምላክ አባት ለሌላቸው ልጆች አባት ነው፤ ባሎቻቸው ለሞቱባቸውም ሴቶች ጠባቂ ነው።


ብርድ የሚከላከልበት ሌላ ምንም ልብስ ስለሌለው ምን ለብሶ ሊያድር ይችላል? እኔ መሐሪ ስለ ሆንኩ እርሱ ወደ እኔ ቢጮኽ እሰማዋለሁ።


አባቶቻችን በጠላት እጅ ተገደሉ፤ ስለዚህ እኛ አባት የሌለን፥ እነሆ እናቶቻችንም ባል አልባ ሆነው ቀርተዋል።


እግዚአብሔር ታዲያ፥ ሌት ተቀን እየጮኹ ለሚለምኑት ሕዝቦቹ አይፈርድላቸውምን? ችላ በማለትስ ርዳታውን ያዘገይባቸዋልን?


እርሱ እናትና አባት ለሌላቸው ድኻ አደጎችና ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች በትክክል ይፈርዳል፤ እርሱ በእኛ ሕዝብ መካከል የሚኖሩትንም መጻተኞች ሁሉ ስለሚወድ ምግብና ልብስ ይሰጣቸዋል።


የዕዳ መሰረዣ ሰባተኛ ዓመት ደርሶአል በማለት ችግረኛ ወገንህን ብድር አትከልክለው፤ እንዲህ ያለ ክፉ ሐሳብም ወደ ልብህ አይግባ፤ ብድር መስጠትን ብትከለክል ችግረኛው ወገንህ ወደ እግዚአብሔር ይጮኻል፤ ስለዚህ በአንተ ላይ እንደ በደል ይቈጠርብሃል።


እርሱ ድኻ በመሆኑ ያን ገንዘብ ለማግኘት በብርቱ ጒጉት ስለሚጠብቅ በየቀኑ የሠራበትን ገንዘብ ፀሐይ ከመጥለቅዋ በፊት ስጠው፤ ባትከፍለው ግን ወደ እግዚአብሔር በመጮኽ ያሳጣሃል፤ አንተም በደለኛ ሆነህ ትገኛለህ።


ይሁን እንጂ በእርሻችሁ ሲያጭዱ ለዋሉት ሠራተኞች ዋጋቸውን ስላልከፈላችሁ እነሆ፥ የተቃውሞ ጩኸታቸው ይሰማል፤ የመከር ሰብሳቢዎቹንም ጩኸት የሠራዊት ጌታ ሰምቶአል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos