መሳፍንት 8:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር የምድያማውያንን መሪዎች ገድላችሁ ድልን እንድትቀዳጁ አድርጓችኋል። ታዲያ እኔ ከዚህ ጋር የሚወዳደር ምን ሠራሁ?” እርሱም ይህን ባለ ጊዜ ቊጣቸው በረደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር የምድያማውያንን መሪዎች ሔሬብንና ዜብን በእጃችሁ አሳልፎ ሰጣችሁ፤ ታዲያ እናንተ ከፈጸማችሁት ጋራ የሚወዳደር ምን ማድረግ እችል ነበር?” ይህን ሲሰሙ ቍጣቸው በረደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር የምድያማውያንን መሪዎች ሔሬብንና ዜብን በእጃችሁ አሳልፎ ሰጣችሁ፤ታዲያ እናንተ ከፈጸማችሁት ጋር የሚወዳደር ምን ማድረግ እችል ነበር?” ይህን ሲሰሙ ቊጣቸው በረደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር የምድያምን አለቆች ሔሬብንና ዜብን በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቶአቸዋል እናንተ ያደረጋችሁትን የሚመስል እኔ ምን ማድረግ እችል ኖርአል?” አላቸው። ከዚህ በኋላ ተዉት፤ ይህን ቃል በተናገራቸውም ጊዜ መንፈሳቸው ዐረፈች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር የምድያምን መኳንንት ሔሬብንና ዜብን በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቶአቸዋል፥ እናንተ ያደረጋችሁትን የሚመስል እኔ ምን ማድረግ እችል ኖሮአል? አላቸው። ይህን በተናገረ ጊዜ ቍጣቸው በረደ። |
እነርሱ ምድርን የወረሱት በሰይፋቸው አይደለም፤ ድል አድርገው የወሰዱትም በራሳቸው ኀይል አይደለም፤ ይህን ሁሉ ያደረጉት አንተ ስለ ወደድካቸውና ከእነርሱም ጋር በመሆን በኀይልህና በብርታትህ ስለ ረዳሃቸው ነው።
ደግሞም እያንዳንዳችሁ እግዚአብሔር በሰጣችሁ እምነት መጠን በትሕትና አስቡ እንጂ ከሚገባችሁ በላይ ስለ ራሳችሁ በትዕቢት አታስቡ ብዬ በተሰጠኝ ጸጋ እነግራችኋለሁ።
ስለዚህ እግዚአብሔር በጸጋው የሰጠንን ልዩ ልዩ ስጦታ በሥራ ላይ እናውል፤ ስጦታችን የእግዚአብሔርን ቃል ማወጅ ከሆነ በእምነታችን መጠን የእግዚአብሔርን ቃል እናውጅ።
በትሕትና ተሞልታችሁ ሌሎች ሰዎች ከእናንተ እንደሚሻሉ አድርጋችሁ ቊጠሩ እንጂ በራስ ወዳድነት ወይም “ያለ እኔ ማን አለ” በሚል ትምክሕት ምንም ነገር አታድርጉ።
እርሱ ግን እንዲህ አላቸው፤ “እኔ ካደረግሁት እናንተ ያደረጋችኹት አይበልጥምን? የእኔ ጐሣ በሙሉ ከሠራው ሥራ የኤፍሬም ሰዎች የሠራችሁት ጥቂቱ ሥራ ይበልጣል። የኤፍሬም ወይን ቃርሚያ ከአቢዔዜር ወይን መከር አይሻልምን?
በዚህም ጊዜ ጌዴዎንና የእርሱ ሦስት መቶ ሰዎች ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ መጥተው ተሻገሩ፤ ድካም ቢሰማቸውም እንኳ አሁንም ጠላትን በማሳደድ ላይ ነበሩ።