ኢያሱ 8:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢያሱና ሠራዊቱ ሁሉ የተሸነፉ በማስመሰል ወደ ኋላ በማፈግፈግ ወደ ምድረ በዳ ሸሹ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢያሱና እስራኤል በሙሉ ድል የተመቱ መስለው በመታየት፣ ወደ ምድረ በዳው ሸሹ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም እስራኤልም ሁሉ ድል የተነሡ መስለው ከፊታቸው በምድረ በዳው መንገድ ሸሹ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በደረሱባቸውም ጊዜ ኢያሱና እስራኤል ሁሉ ከፊታቸው አፈገፈጉ፤ በምድረ በዳው መንገድም ሸሹ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም እስራኤልም ሁሉ ድል የተነሡ መስለው ከፊታቸው በምድረ በዳው መንገድ ሸሹ። |
ለዮሴፍ ዘሮች የተመደበው የምድሪቱ ደቡባዊ ክፍል በኢያሪኮ አጠገብ ከዮርዳኖስ ወንዝ ይጀምራል፤ ይኸውም ከኢያሪኮ ምንጮች ምሥራቃዊ ጫፍ በመነሣት ወደ በረሓው ይዘልቃል፤ ከኢያሪኮም ተነሥቶ ወደ ኮረብታማው አገር በመውጣት እስከ ቤትኤል ይደርሳል።
በሰሜን በኩል የሚገኘውም ድንበራቸው ከዮርዳኖስ ወንዝ ተነሥቶ ወደ ኢያሪኮ ሰሜን ሽቅብ ይወጣና በምዕራብ አቅጣጫ በሚገኘው ኮረብታማ አገር በኩል እስከ ቤትአዌን በረሓ ይደርሳል፤
የዐይ ንጉሥ ይህን በአየ ጊዜ እርሱና የከተማው ሕዝብ እስራኤልን በጦርነት ለመግጠም ወደ ዓራባ ፊት ለፊት ወጡ። ከከተማው በስተጀርባ በኩል የደጀን ጦር መኖሩን አላወቁም ነበር።
በዚህም ጊዜ ብንያማውያን መሸነፋቸውን ተገነዘቡ። ይህም የሆነበት ምክንያት እስራኤላውያን በጊብዓ አካባቢ አስፍረዋቸው በነበሩ የሽምቅ ወታደሮች በመተማመን ወደ ኋላ አፈግፍገው ስለ ነበረ ነው።
ከእስራኤላውያንም ፊት አፈግፍገው ወደ በረሓው ሸሹ፤ ነገር ግን ማምለጥ አልቻሉም፤ በዋናው ሠራዊትና አሁን ከከተማው ውስጥ በመውጣት ላይ ባሉት ወታደሮች መካከል ተይዘው ተደመሰሱ።