La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 24:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እናንተ በማረስ ያልደከማችሁበትን የለማ ምድርና ያልሠራችኋቸውንም ከተሞች መኖሪያ አድርጌ ሰጠኋችሁ፤ እነሆ፥ አሁን ያልተከላችሁትን የወይን ተክልና ያልደከማችሁበትን የወይራ ዛፍ ፍሬ እየተመገባችሁ ትኖራላችሁ።’ ”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ ያልደከማችሁበትን ምድርና ያልሠራችኋቸውን ከተሞች ሰጠኋችሁ። እነሆ፣ በከተሞቹ ትኖራላችሁ፤ ካልተከላችሁት የወይን ተክልና የወይራ ዛፍ ትበላላችሁ።’

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ያልደከማችሁበትንም ምድር፥ ያልሠራችኋቸውንም ከተሞች ሰጠኋችሁ፥ ተቀመጣችሁባቸውም፤ ካልተከላችኋቸውም ከወይንና ከወይራ በላችሁ።’

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ያል​ደ​ከ​ማ​ች​ሁ​በ​ት​ንም ምድር፥ ያል​ሠ​ራ​ች​ኋ​ቸ​ው​ንም ከተ​ሞች ሰጠ​ኋ​ችሁ፤ ተቀ​መ​ጣ​ች​ሁ​ባ​ቸ​ውም፤ ካል​ተ​ከ​ላ​ች​ኋ​ቸ​ውም ከወ​ይ​ንና ከወ​ይራ በላ​ችሁ።’

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ያልደከማችሁበትንም ምድር፥ ያልሠራችኋቸውንም ከተሞች ሰጠኋችሁ፥ ተቀመጣችሁባቸውም፥ ካልተከላችኋቸውም ከወይንና ከወይራ በላችሁ።

Ver Capítulo



ኢያሱ 24:13
7 Referencias Cruzadas  

ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ አወርሳቸው ዘንድ በመሐላ ቃል ኪዳን ወደገባሁባት ምድር አመጣችኋለሁ፤ ርስትም አድርጌ አወርሳችኋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።’ ”


ደግ ሰው ለልጅ ልጆቹ የሚተላለፍ ሀብት ያገኛል፤ የኃጢአተኞችን ሀብት ግን ቅን ሰዎች ይወርሱታል።


“እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር የሚኖሩትን ሕዝቦች ደምስሶ ከተሞቻቸውንና ቤቶቻቸውንም ወርሰህ በዚያ መኖር በምትጀምሩበት ጊዜ፥


እነሆ፥ አምላክህ እግዚአብሔር ወደ መልካሚቱ ለምለም ምድር ሊያስገባህ አምጥቶሃል፤ ያቺም ምድር ከሸለቆዎችና ከኮረብቶች የሚመነጩ ወንዞችና ጅረቶች፥ ፈሳሾች ምንጮችም ይገኙበታል፤


ይሁን እንጂ ኢያሱ ካቃጠላት ከሐጾር በቀር እስራኤላውያን በኮረብታ ላይ የተሠሩ ከተሞችን አላቃጠሉም።


በዚህም ዐይነት እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት የገባው ቃል ኪዳን ሁሉ ተፈጸመ እንጂ አንድም የቀረ የለም።