Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ምሳሌ 13:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ደግ ሰው ለልጅ ልጆቹ የሚተላለፍ ሀብት ያገኛል፤ የኃጢአተኞችን ሀብት ግን ቅን ሰዎች ይወርሱታል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ደግ ሰው ለልጅ ልጆቹ ውርስ ትቶ ያልፋል፤ የኀጢአተኞች ሀብት ግን ለጻድቃን ይከማቻል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ጻድቅ ሰው ለልጅ ልጆቹ ያወርሳል፥ የኃጢአተኛ ብልጥግና ግን ለጻድቅ ትጠበቃለች።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ደግ ሰው ለልጅ ልጅ ያወርሳል፥ የኀጢአተኞች ብልጽግና ግን ለጻድቃን ይደልባል።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 13:22
11 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ ሴቶች ልጆቻችሁን በጋብቻ ለእነርሱ ወንዶች ልጆች አትስጡ፤ እናንተም ለወንዶች ልጆቻችሁ የእነርሱን ሴቶች ልጆች በጋብቻ አትውሰዱ፤ በማንኛውም ጊዜ ከምድሩ መልካም ነገር በልታችሁ ለልጆቻችሁ ዘላቂ ርስት አድርጋችሁ ለማስተላለፍ እንድትችሉ በማንኛውም ጊዜ ከእነርሱ ጋር የወዳጅነት ስምምነት አታድርጉ’ ሲሉ ነግረውን ነበር።


የአገልጋዮችህ ልጆች በሰላም ይኖራሉ፤ ትውልዳቸውም በአንተ ዘንድ ጸንቶ ይኖራል።


የደግ ሰው ልጆች በምድር ላይ ብርቱዎች ይሆናሉ፤ የቅኖች ትውልድ ይባረካል።


የልጆችህን ልጆች ለማየት እንድትበቃ ያድርግህ! ሰላም ከእስራኤል ጋር ይሁን!


ከወጣትነት እስከ ሽምግልና ኖሬአለሁ፤ ታዲያ፥ እግዚአብሔር ደጉን ሰው ሲተወው፥ ልጆቹም ምግብ አጥተው ሲለምኑ፥ ከቶ አይቼ አላውቅም።


የሸመገሉ ሰዎች በልጅ ልጆቻቸው እንደሚመኩ ልጆችም በአባቶቻቸው ይመካሉ።


በአራጣ በማበደርና ሰዎችን በመበዝበዝ የሚከብር ሰው ሀብቱ ሁሉ ለድኾች ልግሥና ለሚያደርግ ሰው ይተላለፋል።


እግዚአብሔር ደስ ለሚያሰኘው ሰው ብቻ ጥበብን፥ ዕውቀትንና ደስታን ይሰጠዋል፤ ለኃጢአተኛ ሰው ግን ድካምን ብቻ ያተርፍለታል፤ ስለዚህም እርሱ ያከማቸውን ሀብት ሁሉ ምንም ላልደከመበት እግዚአብሔርን ደስ ለሚያሰኝ ለሌላ ሰው ትቶለት እንዲያልፍ ያደርገዋል፤ ይህም ሁሉ ከንቱ ስለ ሆነ ነፋስን ለመጨበጥ እንደ መሞከር ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos