ኢያሱ 23:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላካችን እግዚአብሔር እናንተን ለመርዳት በእነዚህ ሕዝቦች ላይ ያደረገውን ሁሉ አይታችኋል፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር ስለ እናንተ ተዋግቶላችኋል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላካችሁ እግዚአብሔር ስለ እናንተ ሲል በእነዚህ ሕዝቦች ሁሉ ላይ ያደረገውን ማንኛውንም ነገር እናንተው ራሳችሁ አይታችኋል፤ ስለ እናንተ የተዋጋላችሁ ራሱ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተም ጌታ አምላካችሁ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ስለ እናንተ ያደረገውን ሁሉ አይታችኋል፤ ስለ እናንተ የተዋጋ እርሱ ጌታ አምላካችሁ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተም አምላካችን እግዚአብሔር በፊታችሁ ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ስለ እናንተ ያደረገውን ሁሉ አይታችኋል፤ ስለ እናንተ የተዋጋ እርሱ አምላካችን እግዚአብሔር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተም አምላካቸሁ እግዚአብሔር በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ስለ እናንተ ያደረገውን ሁሉ አይታችኋል፥ ስለ እናንተ የተዋጋ እርሱ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነው። |
“ ‘እኔ እግዚአብሔር በግብጻውያን ላይ ያደረግኹትንና ንስር ጫጩቶችዋን በክንፎችዋ እንደምትሸከም እኔም እናንተን እስከዚህ ስፍራ እንዴት ወደ እኔ እንዳመጣኋችሁ አይታችኋል፤
ለእነርሱ እንደምሰጣቸው ቃል ወደ ገባሁላቸው ምድር አመጣኋቸው፤ ይሁን እንጂ እነርሱ ከፍተኛ ኰረብቶችንና ለምለም ዛፎችን ባዩ ጊዜ በሁሉም ላይ መሥዋዕት አቀረቡ፤ በሚቃጠል መሥዋዕታቸው፥ መዓዛው በሚጣፍጥ ዕጣናቸውና ለመሥዋዕትም በሚያፈሱት የመጠጥ ቊርባናቸው አስቈጡኝ፤
እንግዲህ በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ ይህን በዐይናችሁ ያያችሁትን ሁሉ እንዳትረሱና ከአእምሮአችሁ እንዳይጠፋ ተጠንቀቁ። ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁም አስተምሩአቸው፤
ንጉሦቻቸውን በእጅህ ይጥልልሃል፤ እነርሱንም ታጠፋና ስማቸው የተረሳ እንዲሆን ታደርጋለህ፤ ማንም ተቋቊሞ ሊገታህ አይችልም፤ ሁሉንም ታወድማለህ።
እግዚአብሔር የሰውን ቃል የሰማበት፥ እንደዚያ ያለ ቀን፥ ከዚያም በፊት ሆነ ከዚያ ወዲህ ታይቶ አይታወቅም፤ በእርግጥም እግዚአብሔር ከእስራኤል ጐን ተሰልፎ ይዋጋላቸው ነበር።
ኢያሱ እነዚህን ነገሥታትና ግዛቶቻቸውን ሁሉ በአንድ ዘመቻ ድል ያደረገው የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለእስራኤል ይዋጋላቸው ስለ ነበረ ነው።
አምላካችሁ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ተስፋ መሠረት ስለ እናንተ ስለሚዋጋ ከእናንተ አንዱ ብቻውን ሆኖ ከእነርሱ ወገን አንዱን ሺህ ማባረር ይችላል፤